የዘ ሄጉ የቀይ ሽብር ችሎት ውሎ | ኢትዮጵያ | DW | 07.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዘ ሄጉ የቀይ ሽብር ችሎት ውሎ

በዘሄግ የሚገኝ አንድ የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት በደርግ ዘመነ መንግስት በተፈጸሙ ወንጀሎች እጃቸው አለበት በሚል የተከሰሱትን ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ሲመለከት ዋለ፡፡ በዛሬው ችሎት አቃቤ ህግ የሰነድ እና የድምጽ ማስረጃዎችን ሲያቀርብ ውሏል፡፡ የመቶ አለቃ እሸቱ ሁለት ጠበቆች ለቀረቡት ማስረጃዎች ምላሽ እንዲሰጡም ዕድል ተሰጥቷቸዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:25
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:25 ደቂቃ

የኔዘርላንድስ አቃቤ ህግ ማስረጃውን አቅርቧል

የኔዘርላንድስ አቃቤ ህግ መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ በተባሉት ተከሳሽ ላይ አራት የጦር ወንጀሎች ክስ መስርቷል፡፡ ተከሳሹ በቀይ ሽብር ወቅት በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር የደርግ መንግስት ተቃናቃኞች “እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩ እና እንዲሰቃዩ” አድርገዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ የኔዘርላንድስ አቃቤ ህግ ተከሳሹ “በነሐሴ 1970 ዓ.ም 75 ወጣት እስረኞች እንዲገደሉ ትዕዛዝ መስጠታቸውን እና አስክሬናቸውም በጅምላ እንዲቀበር ማድረጋቸውን” በክሱ ጠቅሷል፡፡

የመቶ አለቃ እሸቱን ጉዳይ እየተመለከተ የሚገኘው የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት አራት ዳኞች የተሰየሙበት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት ባስቻለው የመጀመሪያ ችሎት የወንጀል ክሱን አስደምጧል፡፡ በሁለተኛው ችሎት ደግሞ ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ እና ከካናዳ የመጡ ስምንት ምስክሮች ቃላቸው ሰጥተዋል፡፡ የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ በስፍራው በመገኘት ከተከታተለው የኢትዮ ሚዲያ ፎረም ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ አቶ ክንፉ አሰፋ ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ፡፡  

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች