የዕርቅና መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴና የዛሬው ችሎት | ኢትዮጵያ | DW | 02.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዕርቅና መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴና የዛሬው ችሎት

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፤ አምና ተይዘው የታሠሩትን የዕርቅና መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎችና አባላት ለመጎብኘት ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ከተጓዙ በኋላ ጥቂቶች እሥረኞቹን ለማየት መቻላቸው ተነግሯል።

የታሠሩት የኮሚቴ መሪዎችና አባላት በዛሬው ዕለት ጉዳያቸው በችሎት እንደሚታይ ቀነ ቀጠሮ ተይዞ እንደነበረ ቢገለጥም፤ ለታኅሳስ 24 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ተመልክቷል። ስለዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የተከሳሾችን የህግ ጠበቃ፤ የህግ ባለሙያ አቶ ተማም አባቡልጉን በስልክ አነጋግረናቸው ነበር።

ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic