የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና በባሕር ዳር | ጤና እና አካባቢ | DW | 19.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና በባሕር ዳር

የባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሃኪም ቤት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ለገጠማቸው ከ1ሺህ 100 በላይ ለሚሆኑ ህሙማን የነፃ የቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ፡፡ ሃኪም ቤቱ ህክምናውን የሚሰጠው ሄማሊያን ካታራክት ከተባለ የአሜሪካ መንግሥት ድርጅት ጋር በመተባበር አንደሆነ ተገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:46

«ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ታክመዋል»

የዓይን ሞራ ግርዶሽ መነሻው የተለያየ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የእድሜ መግፋት ፣ የስኳር ህመምና ሌሎች መድኃኒቶች የሚፈጥሩት የጎንዮሽ ተፅዕኖ መሆኑን መሆኑ ባለሙያዎች ይነገራል። የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ሰሞኑን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እደረገ ነው፡፡ የዓይን ህክምና ስፔሻሊስትና የዓን ሞራ ግርዶሽ ህክምናው ዘመቻ አስተባባሪ ዶ/ር ህይወት ደግነህ ለዶየቼ ቬለ DW እንደገለፁት ከሚያዝያ 7-12/2011 ዓ.ም ባሉት ቀናት 1000 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ህሙማን ለማክም ቢታቀድም ባለፉት 5 ቀናት ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ህክምናውን ማግኘት ችለዋል፡፡

በተመሳሳይ በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ሆስፒታል ባለፈው ሳምንት ከ300 በላይ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ላለባቸው ወገኖች ተመሳሳይ ህክምና መስተቱን የሆስፒታሉ ሥራ አስኪጅ አቶ ይበልታል ጌታ በስልክ ተናግረዋል። ያነጋገርናቸው ታካሚዎች እንዳሉት ለዓመታት በዓይን ብረሀን እጦት መቆየታቸውን አመልክተው በተደረገላቸው ነፃ ህክምና መደሰታቸውን ተናግረዋል። በአማራ ክልል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወገኖች ዝቅተኛ የዓይን ብርሃን ያለባቸው ሲሆን  ከ300 ሺህ በላይ የሚሆኑት  በዓይን ሞራ ግርዶሽ ማየት የማችሉ እንደሁኑ ባለሙያዋ ተናግረዋል። የባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን የጤና ችግሩን ምንነት ማብራሪያ አክሎ ተከታዩን ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

Audios and videos on the topic