ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
"በሕገ ወጥ መንገድ ተሹመናል የሚሉት አካላት” በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ወዳልተፈቀደላቸው የአገልግሎት ቦታዎች በመግባት በቤተክርስቲያኗ ላይ “ሁከት እየተፈጠረ መሆኑን ለመረዳት ችለናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የካቢኔ አባላቶቻቸው በዚህ ጉዳይ እጃቸውን እንዳያስገቡ ማዘዛቸው “መንግሥት ሕግን የማስከበር ኃላፊነቱን ችላ ያለበት ነው” ።
የ86 ዓመቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ይህን ጉዞዋቸዉን ለማድረግ ያቀዱት ከስድስት ወራት በፊት ቢሆንም በአደረባቸዉ የጤና እክል ምክንያት ከእቅዳቸዉ ግማሽ ዓመት ዘግይተዉ ነዉ፤ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፤ ኪንሻሳ የደረሱት። ወደ አንድ ሚሊዮን ነዋሪ እንደሚገኝባት በሚገመተዉ መዲና የኪንሻሳ፤ ፍራንሲስን ለመቀበል በነቂስ ወጥቶም ነበር።
በደቡብ ክልል በመጪው ሳምንት መጀመሪያ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ አሥፈላጊውን መሰናዶ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡ በአሁኑወቅት በህዝበ ውሳኔው ድምፅ ለመስጠት የሚያገለግሉ የምርጫ ቁሳቁሶች ወደ የምርጫ ጣቢያዎች እየደረሱ ሲሆን ለምርጫ አስፈጻሚዎችም በድምፅ አሰጣት ዙሪያ ገለጻ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።፡
ከሰሐራ በርሐ በታች የሚገኙ አገራት ኤኮኖሚ በተያዘው ዓመት በ3.8% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ይፋ አድርጓል። "ያለፈው ዓመት ለክፍለ አኅጉሩ ፈታኝ ነበር" ያሉት የድርጅቱ ዋና ኤኮኖሚስት ፒየር ኦሊቪየ የሩሲያ ጦርነት በዩክሬን፣ የኢነርጂ ቀውስ፣ የዋጋ ንረትን ለመዋጋት የሚደረገው ጥረት ጫና ማሳደራቸውን ተናግረዋል