የዓማዓቱን የልማት ግብ በ2013 | ዓለም | DW | 17.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የዓማዓቱን የልማት ግብ በ2013

የዓማዓቱን የልማት ግብ ከማሳካት አኩዋያ በርካታ የኣፍሪካ ኣገሮች ኣበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸው ተመለከተ። የጸረ ድህነት ግብረ ኃይል የተሰኘው ቡድን ይፋ ባደረገው የ2013 ዓመታዊ ዘገባ በሰረት ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የኣፍሪካ ኣገሮች የዓመዓቱን የልማት ግብ ከማሳካት አኩዋያ የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዟል።

MDG Müttersterblichkeit Sierra Leone

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሜልዴቪስ የመመዘኛ መስፈርቶችን ኣሟልታ ቀዳሚ ስትሆን ዓምና ቁንጮ የነበረችው ካምቦዲያ ደግሞ ሁለተኛ ሆናለች።የተመድ እኣኣ በ2000 ዓም ያጸደቀው ይኸው የዓምዓቱ የልማት እቅድ የሚገባደደው ከሁለት ዓመት በኃላ በ2015 ይሆናል።

የሚሊኒየሙን የልማት ግብ ከማሳካት አኩዋያ ባሳለፍነው ሳምንት ማገባደጃ ይፋ የሆነው የ2013 ዓመታዊ ዘገባ እንደሚያመለክተው ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በርካታ ኣገሮች ኣመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ ናቸው። በነበሩበት የሚዳክሩ የመኖራቸውን ያህል ደግሞ ከደረጃ ዝቅ ብለው የኃሊት የተጘዙ ኣገሮችም እንዳሉ ሪፖርቱ ኣመልክቷል። በሪፖርቱ መሰረት ከሳኃራ በረሃ በታች የሚገኙ 30 የኣፍሪካ ኣገሮችም ኣበረራች ውጤት ኣስመዝግቧል።

የጸረ ድህነት ግብረኃይል የተሰኘው ቡድን ይፋ ያደረገው ይኸው ዘገባ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም ሩዋንዳ ማላዊ ጋና እና ኡጋንዳ በተሻለ ደረጃ የሚሊኒየሙን የልማት ግብ እያሳኩ ከሚገኙ ኣገሮች መካከል ናቸው ተብለዋል።

MDG Indien Bildung 2

የሚሊኒየሙ የልማት ግብ ማለት የተመድ በ2000 ዓም የ189 ኣገሮች ተወካዮች በተገኙበት ያጸደቀው እና በየኣገሮቹ የሚስተዋሉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የአዲሱ ዓመዓት የወል እቅድ ሲሆን እነዚህን እቅዶች ለመመዘንም ስምንት ነጥቦች ያሉት ዓለም ዓቀፍ መመዘኛ ተቀምጦለታል።

ቀድሞ በአዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ እና ኃላም እዚህ በጀርመን ኣገር የሀምቡርግ እና በርሊን ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩት ዶ/ር አለማየሁ ብሩ እንዳብራሩት በስምንቱም መመዘኛዎች የተሟላ ውጤት ያገኘ ኣገር 1 ነጥብ ያገኛል። ግማሽ ያገኙ 0,5 እና ከዚያ በታች ከሆነ ደግሞ 0 እና ኔጋቲቭ ነጥብ ይሰጣቿል።

Menschen aus Uganda Bilder aus Kampala

በዚሁ መሰረት ዓምና 8 ነጥብ በማግኘት ቁንጮ የነበረችው ካምቦዲያ ዘንድሮ ስፍራዋን ለማልዴቪስ ለቃ 7 ነጥብ ይዛ ትከተላለች። ከኣፍሪካ ኣገሮች ደግሞ ሩዋንዳ ከ3 ወደ 6 በመዝለል ደረጃዋን ኣሻሽላ ቀዳሚነቱን ስትይዝ ኢትዮጵያ ደግሞ 5,5 በማግኘት ሁለተኛ ሆናለች።

በመመዘኛው መሰረት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የስኬት ነጥብ ከወረቀት ኣልፎ መሬት ላይ ይታያል ብዬ ኣልገምትም የሚሉት ዶ/ር አለማየሁ በድህነት መለክያ የደረጃ ሰንጠረዥም የዓለም ኣገሮች የበለጸጉ፣ መካከለኛ ገቢ ያላቸው እና ደሃ ተብለው በሶስት እንደሚፈረጁ ጠቅሰው ኢትዮጵያ እጅግ ደኃ ከሚባሉት 187 ኣገሮች መካከልም ሌላው ቀርቶ ከእነሶማሊያ እንኩዋን ዝቅ ብላ 173ኛ መሁኗን ኣስረድቷል። ይህ ማለት በድህነት እርከን በዓለማችን ከኢትዮጵያ በታች የሚፈረጁ ኣገሮች አራት ብቻ ናቸው።

ጃፈር ዓሊ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic