የዓለም የፕረስ ሽልማት ለኢትዮጵያዊዉ ጋዜጠኛ | ኢትዮጵያ | DW | 06.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዓለም የፕረስ ሽልማት ለኢትዮጵያዊዉ ጋዜጠኛ

ባለፈዉ ዓርብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፕረስ ነጻነት ቀን ሲከበር፤ ዋና ጽ/ቤቱ በፓሪስ ፣ ፈረንሳይ የሚገኘው ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) ለቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ

ጋዜጠኛ መሥፍን ነጋሽና ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ታሥረው ለተፈቱት 2 የእስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢዬና ዮሐን ፔርሶን ፤ እ ጎ አ የ 2013 የዓለምን የፕረስ ሽልማት ሰጥቷል። 3 ቱ ጋዜጠኞች ይህ ሽልማት የተሰጣቸው፤ ሐሳብን በነጻ መግለጽና ጋዜጠኝነት በአሸባሪነት በሚያስወነጅልባት ሀገር የጋዜጠኝነትን ኀላፊነት ለመወጣት ላደረጉት ጥረትና ላሳዩት ጽናት መሆኑም ተገልጾአል። ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽን አዜብ ታደሰ በስልክ አግኝታ አነጋግራዉ ነበር

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic