የዓለም የውሃ ቀንና ግድቦች፣ | ጤና እና አካባቢ | DW | 22.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የዓለም የውሃ ቀንና ግድቦች፣

በዓለም ዙሪያ ከ 50 ,000 በላይ ታላላቅ ግድቦች ቢሠሩም አግልግሎታቸው እንዳከራከረ መሆኑ የሚታበል አይደለም። በ 60ኛዎቹና 70ኛዎቹ ዓመታት፣ ግድቦች በብዛት የተሠሩ ሲሆን ፤ በአዳጊ አገሮች ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዘመን ማክተም በኋላ፤

default

የውሃ ግድቦች ተቃውሞ በማርሴይ

ለአዲሶቹ ነጻ ሃገራት ፣ የተፈጥሮ አካባቢ ተንከባካቢ ወገኖች እንደሚሉት፤ ያኔ እንደ መኩራሪያ ቅርስ መታየታቸውም አልቀረም። ግድቦችን ዘለቄታ ያለው ጥቅም እንዲሰጡ አድርጎ መሥራት ይቻላል ወይ? የዶይቸ ቨለ ባልደረባ፣ ሞኒካ ሆዖገን ያቀረበችውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

በማርሴይ ፤ ፈረንሳይ፤ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው የነበሩ ሰልፈኞች፤

« ወንዞች፣ ህይወትን ለመታደግ እንጂ ግድቦች እንዲሠሩባቸው የተፈጠሩ አይደሉም» የሚል መፈክር እስከማሰማት ደርሰው ነበር። ግድብ ሲናድ ሊያስከትል የሚችለውን ጥፋትም ከፕላስቲክ በሠሩት ወሃ መከተሪያ አማካኝነት ለማሳየትም ሞክረዋል። በገሐዳዊው ዓለም መንግሥታት የሚሉትና የሚያደርጉት የተለየ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ የብራዚል መንግሥት ፣ የሚናገር ስለግዙፍ ግድብና የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ አውታር ነው። ተቃዋሚዎች ግን እንደሚባለው እንዳልሆነ ነው የሚያስረዱት ። ለታላላቅ ግድቦች ሥራ፣ ደን በሰፊው ይመነጠራል፤ የሚቋረው ውሃም ሆነ የሚፈጠረው ሰው-ሠራሽ ሀይቅ የወንዙን የውሃ መጠን እንዲቀነስ ያደርጋል። ይህ ደግሞ አሦችና የተለያዩ ነፍሳት እንዲሁም ዕጽዋት ለሚጠፉበት ሁኔታ ሰበብ ይሆናል። በአካባቢ ለዘመናት የኖሩ ተወላጆች፣ አርሶ አደሮች የእርሻ ቦታቸውን እንዲለቁ እየተገደዱም በሌላ ቦታ እንዲሠፍሩ ይደረጋል። በዓለም ዙሪያ በዚህ አኳኋን የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 80 ሚሊዮን ገደማ እንደሚሆን የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ድርጅቶች ያስረዳሉ።

Brasilien indigenes Volk Protest gegen Staudamm Belo Monte

ተቃውሞ በብራዚል

ከመንግሥታት፣የልማትባንኮችናኩባንያዎች፤ባለፈው2011 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት አጥንተው የተስማሙበት፣ Hydropower Sustainability Assessment Protocol የተሰኘው በውሃኃይልኤሌክትሪክየሚያመነጩፕሮጀክቶችንመርማሪቡድንተግባርምምንምይሁንምን፣በተቃዋሚሰልፈኞችአንዳችድጋፍአላገኘም።ግድቦችንበአግባቡበመጠቀም፤ የውሃ ጥራትን እንዲሁም የጤና ይዞታን በመጠበቅ፤ ለአየር ንብረት የሚያስፈልገውን በማከናወንና ሰብአዊ መብትን በማክበር ቀጣይነትያለውየልማት ተግባር ለማከናወን 20 ጉዳዮች መታየት እንዳለባቸው፣ መርማሪው ቡድን ገልጿል። Ami des Terres (የምድር ወዳጅ)የተሰኘው የፈረንሳይ የተፈጥሮ ተንከባካቢ ድርጅት ተወካይ ፣ ራንኮን ሞናቤይ፣ የስምምነቱ ትኩረት በግድቦችና በተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮረ ቢሆንም መሠረታዊ ግቡን ስቷል ባይ ናቸው።

«በመጀመሪያ መመሪያው ደካማ ነው። ሁለተኛ፤ ችግሮችን የሚያከፋፍሉትም ሆኑ የሚያዛምቱት ራሳቸው ኩባንያዎች ናቸው፤ 3ኛ፣ በማንኛውም መለኪያ፣ መካከለኛነት ካለው ዋጋ የሚያሰጥ ደረጃ ላይ እንኳ አልደረሱም። ምን ማለት ነው? የሆነ ነገር ይሠራል፤ ይሁንና የተቆለለው ችግር ሲታይ፣ ፍጹም በቂ አይደለም።»

Wasserkraftwerk Inga I Kongo

የኤልክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በኮንጎ

International Hydropower Association የተሰኘው ማኅበር ሥራ መሪ፣ ሪቻርድ ኤም ቴይለር ፣ የተለየ አስተያየት ነው ያላቸው። እርሳቸው እንደሚሉት መመዘኛው፤ በእርግጥ ድክምት አለበት። ለዚህም ምክንያቱ ራሱ ጉዳዩ እጅግ ከባድ በመሆኑ ነው።

«አንድ ነጠላ ፕሮጀክት ፤ የተጠቀሱትን መለኪያዎች አሟልቶ በከፍተኛ ደረጃ ተፈጻሚነት ያገኛል የሚል ሐሳብ የለኝም። ቀጣይነት ያለው ልማትም ሆነ ዕድገት ማለት ብዙውን ጊዜ ንግድንም ይመለከታል። ተቀዳሚው ጉዳይ፤ ሥራው ያን ያህል ባይሠራም ለመለኪያዎቹ ትኩረት መስጠት የግድ ነው። የተሟላ ውጤት አገኛለሁ ብሎ መጠበቅም አይገባም። ምክንያቱም፤ በገሐድ ተግባር ላይ ውሎ ሊታይ የማይችል ተምኔታዊ ነውና!»

እ ጎ አ በ 1992 ዓ ም፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የተገነባው 52 ሜጋዋት ኤልክትሪክ የሚያመነጨው የ «ኢንጋ » ግድብ ነው። ከ 10 ዓመት በኋላ ኢንጋ 2 ፣ 178 ሜጋዋት፣ አሁን በመሠራት ላይ ያለው ኢንጋ 3 ደግሞ፤ 3,500 ሜጋዋት ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል።

Brasilien Itaipu Staudamm Wasserkraft Wasser Umwelt Umweltschutz

የወንዝ ግድብ በብራዚል

የቶጎ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ሥራ አስኪያጅ Sena Alouka እንዲህ ይላሉ።

«በአሁኑ ዘመን የሚገነቡት ግድቦች፤ ለኤኮኖሚ ልማት ያበረከቱት ድርሻ የለም። የጋናውን አኮሶምቦ ን ያስታውሷል።የኤሌክትሪክ አገልግሎት በፍጹም የማያገኙ የአካባቢውን ማኅብረሰብ አባላት ይዞታ ማጤንም ይቻላል። ኮንጎ፤ በአፍሪቃ አጅግ ግዙፉን ግድብ ሠርታለች። ይሁን እንጂ በዛ ያሉ ዜጎቿ ጨለማ የዋጣቸው ናቸው።»

እንደ አሉካ አባባል፤ ግድቦች፤ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ እስከሆነ ድረስ፣ አፍሪቃ፣ ያልቃል በማይባለው መጠነ ሰፊ የፀሐይና ነፋስ ኃይል መጠቀሙ ይበጃታል።

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 22.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14PO0

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 22.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14PO0