የዓለም የእግር ኳስ ፌደሬሽን ቅሌትና ምርጫው | ስፖርት | DW | 29.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የዓለም የእግር ኳስ ፌደሬሽን ቅሌትና ምርጫው

ትናንትና ዛሬ ፤ የዓለም የእግር ኳስ ፌደሬሽን (FIFA) በዋና ማዕከሉ በ Zürich እስዊትስዘርላንድ ኮንግረስ በማካሄድ ላይ ሲሆን፤ በዋዜማው አካባቢ በጉቦኛነት ተጠርጥረዋል የተባሉ 7 የማሕበሩ ሠራተኞች ለምርመራ በስዊዝ ፖሊስ ተይዘው በእሥር ላይ ይገኛሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ የፍትሕ ጉዳይ ሚንስቴር ፤ 14 ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ባለሥልጣናትንም ሆነ ንግድ ሥራ አስኪያጆችን በጉቦ ሳቢያ ከሷል። የአውሮፓ የእግር ኳስ ማሕበር (UEFA)ፕሬዚዳንት ፤ የቀድሞው የfr,ንሳይ ብሔራዊ ቡድን ታዋቁቂ ተጫዋች፤ ሚሸል ፕላቲኒ ፣ የFIFA ፕሬዚዳንት ዜፕ ባላተር ሥልጣን መልቀቅ ይገባቸዋል እስከማለት ደርሷል ። FIFA ፈጸመ ስለተባለው የቅሌት ተግባርም ሆነ ጉቦኛነት እንዲሁም ብላተር ለቀጣይ የአመራር ዘመን ዝግጁ ስለመሆናቸው የተጠናቀረ ዘገባ አለን።

በዓለም የእግር ኳስ ፌደሬሽን(FIFA) ማዕከል በዙሪኽ፣ ከ 17 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ወዲህ እንደገና በዛሬው ስብሰባ ለምርጫ የቀረቡት የ 79 ዓመቱ አዛውንቱ የእስዊስ ተወላጅ ዜፕ ብለተር ፣ ገና ለመወዳደር ሲዘጋጁ ፤ «ገና ተልእኮየን አላሳካሁምና በተጫማሪ ለቀጣይ 4 ዓመታት መሥራት እፈልጋለሁ» ማለታቸው የሚታወስ ነው። ሰሞኑን የተራገበውን ጉቦኛነት በተመለከተ «የማህበሩ ስም ሲጠፋ ዝም ብለን አንመለከትም» ነው ያሉት።

ከተያዙት 7 ሠራተኞች መካከል፤ 2 ቱ ምክትል የ FIFA ፕሬዚዳንቶች የነበሩ ናቸው። የእስዊስ የሕግና ፍትሕ ጉዳይ ባለሥልጣናት ሩሲያና ቐጠር እ ጎ አ በ 2018 እና በ 2022 እንዲያዘጋጁ ዕድል የተሰጣቸው በጉቦ ሳይሆን አልቀረም የሚል ጥርጣሬ እንዳደረባቸው ነው የገለጡት።

ባለፉት 20 ዓመታት ፣ እንዲያውም፣ 150 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ ፣ የድምጽ ድጋፍ ለማግኘት በጉቦ መልክ ሳይሰጥ አልቀረም ነው የተባለው። ውድድር የማዘጋጀት ዕድል ሲገኝ ፤ ኩባንያዎች፣ ጨዋትን በቴሌቭዥን የማስተላለፍ ልዩ መብት እንዲሁም በዚህ ረገድ ንግድ እንዲያካሂዱ አጋጣሚ ሳይፈጥርላቸው እንዳልቀረ ተመልክቷል።በ FIFA ሙስና ለአያሌ ዓመታት ደርቶ መቆየቱን የፈረንሳይ ውጭ ጉድይ ሚንስትር ሎራ ፋቢዩስ ተናግረዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በበኩላቸው ፤ ብለተርንና FIFA ን በመደገፍ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በ FIFA የውስጥ ጉዳይ ጣቃል እየገባች ነው ሲሉ ከመውቀሳቸውም፤ « የዚህ ዓይነቱ እንቅሥቃሴ ዓላማ፣ የ 2018 ቱ ውድድር በሩሲያ እንዳይካሄድ ፤ እንዲሠናከል ለማድረግ በማሠለሰል ላይ ያተኮረ ነው « ነው ሲሉ ነቅፈዋል።

ብላተር ሥልጣን እንዲለቁ በተለይ ከ UEFA በኩል ግፊት በተጠናከረበት በዚህ ወቅት፤ በሚካሄደው ምርጫ ፤ የ FIFA ው መሪ ከአፍሪቃው ክፍለ ዓለም፤ 54 የድምፅ ድጋፍ የሚያገኙ በመሆናቸው የሚያሠጋቸው ሁኔታ አይኖርም ነው የተባለው። ተፎካካሪአቸው የዮርዳኖሱ ልዑል ዓሊ ቢን ኧል ሁሴይን መሆናቸው የታወቀ ነው። ዜፕ ብላተር ፣ ለአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ምን አደረጉና ነው ያን ያህል ጠንካራ ድግፍ የሚሰጣቸው? DW ያነጋገረው የካቡ ቨርድ ው ጋዜጠኛ ዳንኤል አልሜይዳ እንዲህ ይላል።

«ብዙዎቻችን የምናስበው፤ ዓለም ፣ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ደረጃ ባለፉት ዓመታት ከፍ ባለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ዕውቅና እንዲሰጠው አስተዋጽዖ ካደረጉት መካከል፣ ብላተር ይጠቀሳሉ። በዓለም ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉ የአፍሪቃ ቡድኖች፤ ቁጥር እንዲጨምር ዕድል የተሰጠውም በብላተር የአስተዳደር ዘመን ነው። የአፍሪቃ እግር ኳስ ጥራት እንዲኖረውም ብዙ ወጪ ተድርጓል።»

«ጎል በተሰኘው የ FIFA መሠረታዊ የልማት መርኀ ግብር ፤ ካቡ ቨርደ ምን ዕይነት ጠቀሜታ አገኘች?

« እስከ 2007 (እ ጎ አ ) ፤ ካቡ ቨርደ ውስጥ ሣር የለበሰ አንድም ስታዲየም አልነበረም። በአሁኑ ጊዜ 17 በሰው ሠራሽ ዘዴ ፤ ልዩ ሣር የለበሱ 17 የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች አሉን፤ በ FIFA ገንዘብ የተደገፈና የምሥክር ወረቀትም የተሰጠው ነው።»

ይህንና የመሳሰለውን በማድረግ ብላተር ከአፍሪቃውያን የአግር ኳስ ክለቦች ተወዳጅነትንናn ተዓማኒነትን ለማትረፍ በቅተዋል።

የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር እ ጎ አ በ 2010 ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ እንዲዘጋጅ፤ ባላተር በትጋት ሠርተዋል ተብለው እስካሁን በአፍሪቃውያን ዘንድ ይመሠገናሉ።ደቡብ አፍሪቃ በጉቦ ነው ያን ዕድል ያገኘች የሚል ዘለፋ አሁን በመሰንዘሩ የተናደዱት፤ የደቡብ አፍሪቃ የእስፖርት ሚንስትር ፊኪሌ እምባሉላ ፣ በፍጹም የተባለው ጉዳይ በእኛ ሕዝብና መንግሥት አልተቃጣም ነው ያሉት።

«በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ሥም፣ ገንዘብ የሚባል ነገር በጭራሽ ለማንም ግለሰብ ለሚሰኝ አላስተላለፍንም። የ FIFA 2010 ዋንጫ ውድድርን በተመለከተ፣ በፈጠራ እንደተነገረው መንግሥታችንን ከጉቦ መስጠት ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም። ይህ አፍራሽ ተልእኮ ያለው ከንቱ ክስ ነው።»

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች