1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ አንድ ሳምንት፣

ረቡዕ፣ ሰኔ 11 2006

ከማራኪ ጨዋታ ጋር በሰፊ ብልጫ ተጋጣሚዎቻቸውን ፤ ሆላንድ እስፓኝን፣ 5-1 ፣ ጀርመን ፖርቱጋልን 4-0 ያሸነፉበት ሁኔታ በኳስ ጨዋታ ተመልካቾችና ሐያስያን በሰፊው ሲወሳ ፣ የሌሎቹ ያን ያህል አድናቆት አልተቸረውም።

https://p.dw.com/p/1CLcf
ምስል Reuters

የአፍሪቃ ብሔራዊ ቡድኖች ደግሞ ፤ ከአይቮሪኮስት በስተቀር ሌሎቹ 4ቱ ፤ ማለትም አልጀሪያ ፣ ናይጀሪያ ጋናና ካሜሩን በመጀመሪያ ግጥሚያዎቻቸው ፤ ኳስ አፍቃሪውን የአፍሪቃን ህዝብ አላረኩም። በቀጣዩ ግጥሚያቸው የማሸነፍ ዕድላቸው ደግሞ የጨፈገገ ነው የሚመስለው። ስለዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ፤ በተለይም ስለአፍሪቃያኑ ብሔራዊ ቡድኖች አጨዋወት--

FIFA Fußball WM 2014 Brasilien Mexiko Neymar Ochoa
ምስል Reuters

በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም የኳስ አፍቃሪው ቁጥር እጅግ እየጨመረ በተገኘበት በአሁኑ ሰዓት፤ በብራዚል አፍሪቃን ወክለው ከተገኙት አገሮች መካከል ፤ ለምሳሌ ያህል የናይጀሪያንና የኢራንን ጨዋታ በአጠቃላይ ከ 25 ሚሊዮን በላይ አፍሪቃውያን ጎልማሶች ናቸው በቴሌቭዥን የተከታተሉት። ሆኖም ፣ ናይጀሪያ ከኢራን ጋር ባዶ ለባዶ መለያየቷ፣ ጋናውያን ፤ የጨዋታ ችሎታም ሆነ ጥንካሬ ሳያንሳቸው በዩናይትድ ስቴትስ 2-1 መሸነፋቸው፣ አልጀሪያ ትናንት ጥሩ ጀምራ ፣ በቤልጅግ ተሸንፋ መውጣቷ ፣ ካሜሩን በሜክሲኮ 1-0 መረታቷ ፤ ከአፍሪቃውያን ኳስ አፍቃሪዎች የሚጠበቅ አልነበረም።

ለዓለም ዋንጫ ወደ ብራዚል ከማለፋቸው በፊት እዚህ ጀርመን ውስጥ ካሜሩናውያን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነትም ቢሆን ባደረጉት ግጥሚያ ችሎታቸውን በማሥመስከር፣ ሊያሸነፍም ይችሉ ነበር፣ ይሁንና 2-2 መለያየታቸው የሚታወስ ነው፦ ይሁን እንጂ ያን ጥንካሬ በብራዚል አለማሳየታቸው፣ በጠንካራው የጀርመን ቡድን ላይ ከወዲሁ የፎከሩት ጋናውያንም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ እንደሚጠበቅባቸው ሆነው አለመገኘታቸው---ከሞላ ጎደል በሁሉም ላይ ምን ነካቸው የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ምን ይሆን ችግሩ ? ዶክተር ተስፋዬ ጥላሁን---

ከእግር ኳስ ጨዋታው ውድድር ጋር ተያይዞ በመገናኛ ብዙኀን የሚካሄደው የሥነ ልቡና ጦርነት መሰሉ ሐተታ የሚያስገርም ነው። አንድ ኃይለኛ ሜክሲካዊ በረኛ ፤ የብራዚልን የግብ ተደጋጋሚ ሙከራ ማክሸፉ ፣ አስተጋጂዋ አገር አከተመላት የሚያሰኝ ይሆናል ወይ? የኔደርላንድና የጀርመን ቡድኖች በሰፊ ብልጫ ማሸነፋቸው፣ ለዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ደረሱ ማለት አይደለም ። የእግር ኳስ ባለሙያው ምን ይላል? ዶ/ተስፋዬ--

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ