የዓለም የኤድስ ቀን | ጤና እና አካባቢ | DW | 02.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

የዓለም የኤድስ ቀን

በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል ባለፈው እሁድ ከ3,383 በላይ ሰዎች በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረጋቸው ተሰምቷል።በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የኤድስ ጉዳይ ቢሮ እንዳስታወቀው በዕለቱ ሁለት ሺ ሰዎች ለመመርመር ነበር የታቀደዉ።

ይሁንና ከታቀደዉ በላይ ሰዉ በፈቃደኝነት ተመርምሯል።አሶሺየትድ ፕረስ የተሰኘዉ ዜና አገልግሎት እንደዘገበዉ ከሆነ ከጋምቤላ መስተዳድር ሕዝብ 6.5 በመቶዉ ከኤች.አይ.ቪ. ጋር ነዉ የሚኖረዉ። የዛሬዉ ጤናና አካባቢ ትናንት የዋለዉን የዓለም ኤድስ ቀን አስታኮ የኢትዮጵያን ሁኔታ ይቃኛል።እሸቴ በቀለ አጠናቅሮታል።

አቶ ብርሃኑ አለሙ የስነ-ልቦና አማካሪ ባለሙያ ናቸው። በኢትዮጵያ የኤድስ መረጃ ማዕከል በ952 ነጻ የስልክ መስመር ወገን ኤድስ ቶክ ላይን በተባለ አገልግሎት በየእለቱ በስነ-ተዋልዶ ጤና፤ኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ጉዳዮች ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣሉ። በስልክ ሙያዊ ግልጋሎታቸውን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ከሚያነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአባላዘር በሽታዎች፤ቲቢ ፤ ኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ይገኙበታል።አቶ ብርሃኑ በወገን ኤድስ ቶክ ላይን የ952 ነጻ የስልክ መስመር ባገለገሉባቸው አመታት የተጠየቋቸውን ጥያቄዎች መለስብ ብለው ሲመለከቱ ለውጥ መኖሩን ይናገራሉ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም መረጃ መሰረት እ.ኤ.አ. በ2014 ከ35 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከኤች.አይ.ቪ. ተህዋሲ ጋር ይኖራሉ። ከእነዚህ መካከል 1.2 ሚሊዮን ያህሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በየአመቱ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች በኤድስና ተያያዥ ምክንያቶች ይሞታሉ። ከዚህ ቁጥር መካከል 47,000 ያህሉ በኢትዮጵያ ይገኛል። እ.ኤ.አ. በ2012 ከ 170,000 በላይ ህጻናት ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ። ከ 900,000 በላይ ህጻናት ደግሞ ወላጆቻቸውን በዚሁ ምክንያት አጥተዋል።
በዚህ ሳምንት የዓለም ኤድስ ቀን ሲከበር ከበሽታው ነጻ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር ትኩረት፤መተባበር እና ማሳካት ያስፈልጋል የሚል መርህ ነበረው። የኤች.አይ.ቪ. ተህዋሲ እና እሱን ተከትሎ የሚፈጠረው ኤድስ ላለፉት በርካታ አመታት የዓለም ራስ ምታት ሆኖ ቆይቷል። ዘንድሮ ህዳር 22 የዓለም ኤድስ ቀን ሲከበር ግን ለዘመናት የዘለቀው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ቀለል ያለ ይመስላል። ዓለምም ከኤድስ ነጻ ትውልድ ይኖራል ብሎ ማለም ጀምሯል-ቢያንስ በመፈክር ደረጃ።
ናማራ ዋረን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ አስተባባሪ ናቸው። ዋረን ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት የኤች.አይ.ቪ. ስርጭትን በመቀነስ፤የህክምና አገልግሎቱን በማቅረብ እና ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ እድሉን በመቀነስ ከፍ ያለእምርታ ማስመዝገቧን ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል ባለፈው እሁድ ከ3,383 በላይ ሰዎች በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረጋቸው ተሰምቷል።በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የኤድስ ጉዳይ ቢሮ እንዳስታወቀው በዕለቱ ሁለት ሺ ሰዎች ለመመርመር ነበር የታቀደዉ። ይሁንና ከታቀደዉ በላይ ሰዉ በፈቃደኝነት ተመርምሯል።አሶሺየትድ ፕረስ የተሰኘዉ ዜና አገልግሎት እንደዘገበዉ ከሆነ ከጋምቤላ መስተዳድር ሕዝብ 6.5 በመቶዉ ከኤች.አይ.ቪ. ጋር ነዉ የሚኖረዉ። የዛሬዉ ጤናና አካባቢ ትናንት የዋለዉን የዓለም ኤድስ ቀን አስታኮ የኢትዮጵያን ሁኔታ ይቃኛል።እሸቴ በቀለ አጠናቅሮታል።
አቶ ብርሃኑ አለሙ የስነ-ልቦና አማካሪ ባለሙያ ናቸው። በኢትዮጵያ የኤድስ መረጃ ማዕከል በ952 ነጻ የስልክ መስመር ወገን ኤድስ ቶክ ላይን በተባለ አገልግሎት በየእለቱ በስነ-ተዋልዶ ጤና፤ኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ጉዳዮች ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣሉ። በስልክ ሙያዊ ግልጋሎታቸውን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ከሚያነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአባላዘር በሽታዎች፤ቲቢ ፤ ኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ይገኙበታል።አቶ ብርሃኑ በወገን ኤድስ ቶክ ላይን የ952 ነጻ የስልክ መስመር ባገለገሉባቸው አመታት የተጠየቋቸውን ጥያቄዎች መለስብ ብለው ሲመለከቱ ለውጥ መኖሩን ይናገራሉ።
ድምጽ 1 አቶ ብርሃኑ አለሙ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም መረጃ መሰረት እ.ኤ.አ. በ2014 ከ35 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከኤች.አይ.ቪ. ተህዋሲ ጋር ይኖራሉ። ከእነዚህ መካከል 1.2 ሚሊዮን ያህሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በየአመቱ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች በኤድስና ተያያዥ ምክንያቶች ይሞታሉ። ከዚህ ቁጥር መካከል 47,000 ያህሉ በኢትዮጵያ ይገኛል። እ.ኤ.አ. በ2012 ከ 170,000 በላይ ህጻናት ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ። ከ 900,000 በላይ ህጻናት ደግሞ ወላጆቻቸውን በዚሁ ምክንያት አጥተዋል።
በዚህ ሳምንት የዓለም ኤድስ ቀን ሲከበር ከበሽታው ነጻ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር ትኩረት፤መተባበር እና ማሳካት ያስፈልጋል የሚል መርህ ነበረው። የኤች.አይ.ቪ. ተህዋሲ እና እሱን ተከትሎ የሚፈጠረው ኤድስ ላለፉት በርካታ አመታት የዓለም ራስ ምታት ሆኖ ቆይቷል። ዘንድሮ ህዳር 22 የዓለም ኤድስ ቀን ሲከበር ግን ለዘመናት የዘለቀው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ቀለል ያለ ይመስላል። ዓለምም ከኤድስ ነጻ ትውልድ ይኖራል ብሎ ማለም ጀምሯል-ቢያንስ በመፈክር ደረጃ።
ናማራ ዋረን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ አስተባባሪ ናቸው። ዋረን ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት የኤች.አይ.ቪ. ስርጭትን በመቀነስ፤የህክምና አገልግሎቱን በማቅረብ እና ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ እድሉን በመቀነስ ከፍ ያለእምርታ ማስመዝገቧን ይናገራሉ።

«እ.ኤ.አ. በ2001 በከተሞች የሚታየው የኤች.አይ.ቪ. ስርጭት 14 በመቶ ነበር።እ.ኤ.አ. በ2012 ይህ ቁጥር ወደ 4.4 በመቶ ቀንሷል። በገጠር አካባቢዎች ሁለት በመቶ የነበረው ወደ 1.8 በመቶ ቀንሷል። በኤች.አይ.ቪ. የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በ2010 25 ሺ የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2013 ወደ 21 ሺ ዝቅ ብሏል። ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። አጠቃላይ የስርጭት መጠኑም ወደ 1.2 በመቶ አካባቢ ነው። አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት የሚያገኙ፤በፈቃደኝነት የምክርና የምርመራ የያደርጉ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው። አሁን በሃገሪቱ በተዘረጋው አገልግሎት መድሃኒት የፈለገ ማግኘት ይችላል። ይህ ብዙ ሰዎች በህይወት መቆየትና ለኢኮኖሚው ማበርከት እንዲችሉ አድርጓል። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ተህዋሲው ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ እድሉን ለመቀነስ የሚሰው አገልግሎት ሽፋን እየጨመረ ነው። በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ሃያ ሺ አሁን ወደ 40 ሺ አካባቢ ዝቅ ብሏል።ስለዚህ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ ተመዝግቧል። ይህን ማስቀጠል ይኖርብናል።»
በኢትዮጵያ የብሔራዊኤች.አይ.ቪ/ኤድስመከላከያ እና መቆጣጠሪያ ካውንስል ጨምሮ በርካታ አገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት በዚህ ጉዳይ ላይ ይሰራሉ። በኢትዮጵያ የኮንዶ አገልግሎትን በማስተዋወቅና አጠቃቀምና ጠቀሜታውን በማስተማር ረገድ ከፍ ያለ ሚና ከተጫወቱ ተቋማት መካከል ዲኬቲ ኢትዮጵያ ይጠቀሳል። በዲኬቲ ኢትዮጵያ የብሄራዊ ሽያጭ አገልግሎት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፋሲል ጉተማ ኢትዮጵያውያን ስለ ኮንዶም በግልጽ መነጋገር መወያየትና የመጠቀም ባህሉ መጨመሩን ያስረዳሉ። የስነ-ልቦና አማካሪ ባለሙያው አቶ ብርሃኑ አለሙም ኮንዶም የመጠቀም ባህሉ ማደጉን፤በፈቃደኝነት የመመርመር ፍላጎትም ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ልብ ብለዋል። ነገር ግን የምርመራ ግልጋሎቱ ላይ ክፈተት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥያቄዎች ለአቶ ብርሃኑ ይቀርቡላቸዋል።

Infografik Todesfälle aufgrund von AIDS 2013 Englisch

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ አስተባባሪው ናማራ ዋረን በአንዳንድ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ክፍተት ሊኖር ቢችልም በሂደት ለውጥ ይመጣል ብለው ያምናሉ።
«ሁሉንም ነገር ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ማየት ይኖርብናል። ለኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች ከሌሎቹ እኩል ይገኛሉ። አሁን ለምሳሌ ለውስብስብ የሳንባ ህመም ህክምና መስጫ አለን? የለንም። ስለዚህ ለኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ህክምና የሚያስፈልጉ አገልግሎቶችም ከአጠቃላይ የጤናው ዘርፍ እድገት ጋር የሚለወጥ ይሆናል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት መሰረታዊ መድሃኒቶችና የህክምና እገዛ ሲፈልጉ ማግኘት እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል። ለምሳሌ በክልሎችና በአዲስ አበባ በሚገኙ ማዕከሎችም ልዩነት ይታያል። አዲስ አበባ ከጋምቤላ የተሻለ የህክምና መስጫ ማዕከሎች አሏት። ዋናው ነገር በክልል እና ማዕከላዊ መንግስት ህክምናውን ለሚፈልጉ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል። የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ የሚፈልጉ መመርመር አሊያም ኮንዶም ለመጠቀም የሚሹ አገልግሎቱን እያገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ።»
አቶ ብርሃኑ አለሙ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ምክርና የደም ምርመራ እና የህክምና አገልግሎት መስፋፋት አሁን ለተፈጠረው ለውጥ ከፍ ያለ ጥቅም አለው ይላሉ። ሆኖም አሁን ለኤች.አይ.ቪ. ተህዋሲና ስለ ኤድስ ያለው ግንዛቤ መዘናጋት እንዳይፈጥር ስጋት አለኝ ይላሉ። ናማራ ዋረን የኤች.አይ.ቪ እና ኤድስን ስርጭት ከዚህ በላይ ለመግታትም ሆነ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውን ለመቀነስ ብሎም ነጻ የሆነ ትውልድ መፍጠር ይቻላል ባይ ናቸው። ነገር ግን መመርመርን በቅድመ ሁኔታነት ያስቀምጣሉ። «እያንዳንዱ ግለሰብ በመመርመር ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ ይኖርባቸዋል። መንግስት አገልግሎቱን ያቀርባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የመሳሰሉ አለም አቀፍ ተቋማት ይደግፋሉ። ሄዶ መመርመር ግን ግለሰባዊ ውሳኔ ነው። በመርመር ራስን እና የሚወዱትን ሰው መጠበቅ ይቻላል። ትዳር ከመመስረት በፊትም በመርመር የትዳር አጋርን እና የሚወልዱትን ልጅ መጠበቅ ይቻላል። »
«እ.ኤ.አ. በ2001 በከተሞች የሚታየው የኤች.አይ.ቪ. ስርጭት 14 በመቶ ነበር።እ.ኤ.አ. በ2012 ይህ ቁጥር ወደ 4.4 በመቶ ቀንሷል። በገጠር አካባቢዎች ሁለት በመቶ የነበረው ወደ 1.8 በመቶ ቀንሷል። በኤች.አይ.ቪ. የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በ2010 25 ሺ የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2013 ወደ 21 ሺ ዝቅ ብሏል። ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። አጠቃላይ የስርጭት መጠኑም ወደ 1.2 በመቶ አካባቢ ነው። አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት የሚያገኙ፤በፈቃደኝነት የምክርና የምርመራ የያደርጉ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው። አሁን በሃገሪቱ በተዘረጋው አገልግሎት መድሃኒት የፈለገ ማግኘት ይችላል። ይህ ብዙ ሰዎች በህይወት መቆየትና ለኢኮኖሚው ማበርከት እንዲችሉ አድርጓል። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ተህዋሲው ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ እድሉን ለመቀነስ የሚሰው አገልግሎት ሽፋን እየጨመረ ነው። በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ሃያ ሺ አሁን ወደ 40 ሺ አካባቢ ዝቅ ብሏል።ስለዚህ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ ተመዝግቧል። ይህን ማስቀጠል ይኖርብናል።»

በኢትዮጵያ የብሔራዊኤች.አይ.ቪ/ኤድስመከላከያ እና መቆጣጠሪያ ካውንስል ጨምሮ በርካታ አገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት በዚህ ጉዳይ ላይ ይሰራሉ። በኢትዮጵያ የኮንዶ አገልግሎትን በማስተዋወቅና አጠቃቀምና ጠቀሜታውን በማስተማር ረገድ ከፍ ያለ ሚና ከተጫወቱ ተቋማት መካከል ዲኬቲ ኢትዮጵያ ይጠቀሳል። በዲኬቲ ኢትዮጵያ የብሄራዊ ሽያጭ አገልግሎት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፋሲል ጉተማ ኢትዮጵያውያን ስለ ኮንዶም በግልጽ መነጋገር መወያየትና የመጠቀም ባህሉ መጨመሩን ያስረዳሉ። የስነ-ልቦና አማካሪ ባለሙያው አቶ ብርሃኑ አለሙም ኮንዶም የመጠቀም ባህሉ ማደጉን፤በፈቃደኝነት የመመርመር ፍላጎትም ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ልብ ብለዋል። ነገር ግን የምርመራ ግልጋሎቱ ላይ ክፈተት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥያቄዎች ለአቶ ብርሃኑ ይቀርቡላቸዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ አስተባባሪው ናማራ ዋረን በአንዳንድ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ክፍተት ሊኖር ቢችልም በሂደት ለውጥ ይመጣል ብለው ያምናሉ።
«ሁሉንም ነገር ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ማየት ይኖርብናል። ለኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች ከሌሎቹ እኩል ይገኛሉ። አሁን ለምሳሌ ለውስብስብ የሳንባ ህመም ህክምና መስጫ አለን? የለንም። ስለዚህ ለኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ህክምና የሚያስፈልጉ አገልግሎቶችም ከአጠቃላይ የጤናው ዘርፍ እድገት ጋር የሚለወጥ ይሆናል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት መሰረታዊ መድሃኒቶችና የህክምና እገዛ ሲፈልጉ ማግኘት እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል። ለምሳሌ በክልሎችና በአዲስ አበባ በሚገኙ ማዕከሎችም ልዩነት ይታያል። አዲስ አበባ ከጋምቤላ የተሻለ የህክምና መስጫ ማዕከሎች አሏት። ዋናው ነገር በክልል እና ማዕከላዊ መንግስት ህክምናውን ለሚፈልጉ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል። የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ የሚፈልጉ መመርመር አሊያም ኮንዶም ለመጠቀም የሚሹ አገልግሎቱን እያገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ።»
አቶ ብርሃኑ አለሙ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ምክርና የደም ምርመራ እና የህክምና አገልግሎት መስፋፋት አሁን ለተፈጠረው ለውጥ ከፍ ያለ ጥቅም አለው ይላሉ። ሆኖም አሁን ለኤች.አይ.ቪ. ተህዋሲና ስለ ኤድስ ያለው ግንዛቤ መዘናጋት እንዳይፈጥር ስጋት አለኝ ይላሉ።
ናማራ ዋረን የኤች.አይ.ቪ እና ኤድስን ስርጭት ከዚህ በላይ ለመግታትም ሆነ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውን ለመቀነስ ብሎም ነጻ የሆነ ትውልድ መፍጠር ይቻላል ባይ ናቸው። ነገር ግን መመርመርን በቅድመ ሁኔታነት ያስቀምጣሉ።
«እያንዳንዱ ግለሰብ በመመርመር ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ ይኖርባቸዋል። መንግስት አገልግሎቱን ያቀርባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የመሳሰሉ አለም አቀፍ ተቋማት ይደግፋሉ። ሄዶ መመርመር ግን ግለሰባዊ ውሳኔ ነው። በመርመር ራስን እና የሚወዱትን ሰው መጠበቅ ይቻላል። ትዳር ከመመስረት በፊትም በመርመር የትዳር አጋርን እና የሚወልዱትን ልጅ መጠበቅ ይቻላል። »

እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic