የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ ቅኝት | ዓለም | DW | 28.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ ቅኝት

በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የተሳተፈበት የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ ከተጠናቀቀ ቀናት አለፉ። በጉባኤው የዓለም መሪዎች፣ ባለወረቶች እና በተለያዩ ማኅበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ-ሐብታዊ ጉዳዮች ለውጥ የሚሹ አራማጆች ተሳትፈው ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 12:12

የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ ቅኝት

በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የተሳተፈበት የዓለም የኤኮኖሚ ጉባኤ ከተጠናቀቀ ቀናት አለፉ። በጉባኤው የዓለም መሪዎች፣ ባለወረቶች እና በተለያዩ ማኅበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ-ሐብታዊ ጉዳዮች ለውጥ የሚሹ አራማጆች ተሳትፈው ነበር። የሕግ ባለሙያዋ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ የትነበርሽ ንጉሴ በዚያው መድረክ ተገኝታ ነበር። 
በመድረኩ የተሳተፉት ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዘጠኝ ወራት ገደማ በፊት ኢትዮጵያ ለመፍረስ ከሚያደርስ ሥጋት ውስጥ እንደነበረች በዚያው ጉባኤ ተናግረው ነበር። 
ጠቅላይ ምኒስትሩ እንዳሉት ዜጎች ላነሱት ፖለቲካዊ እና ምጣኔ-ሐብታዊ ጥያቄ መንግሥት የሰጠው ምላሽ ወደ አደገኛ ምዕራፍ አድርሷት እንደነበር ገልጸዋል።  ጠቅላይ ምኒስትሩ በአመራሮች መካከል አለ ያሉት ደካማ የርስ በርስ ግንኙነት ጉዳዩን የበለጠ አደገኛ እንዳደረገውም በዳቮሱ ጉባኤ ለታደሙ ነግረዋቸዋል። በተሳሳተ መንገድ መረዳት፤ አለመተማመን እና እርስ በርስ መጠራጠር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሒቃን ዘንድ መታየቱንም ገልጸዋል። የዛሬው የማኅደረ ዜና መሰናዶ የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድን ንግግር ጨምሮ የዳቮሱ ጉባኤ ያነሳቸውን አበይት ጉዳዮች ይቃኛል። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ 
ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic