የዓለም የስደተኞች ቀን | ኢትዮጵያ | DW | 20.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዓለም የስደተኞች ቀን

በየአገራቸዉ ከሚካሄደዉ ጦርነት ወይም ከሚደርስባቸዉ ጥቃት፤ ሸሽተዉ ወደሌላ ለመሰደድ የተገደዱ ሰዎች ቁጥር ላለፉት 15ዓመታት በከፍተኛ መጠን እንደጨመረ የተመድ ዛሬ አመለከተ።

default

ድርጅቱ ዓለም ዓቀፍ የስደተኞች ቀን በሚታሰብበት በዚህ ዕለት ይፋ እንዳደረገዉ ባለፈዉ የአዉሮጳዉያኑ ዓመት የተፈናቃይ ሕዝብ ቁጥር 43,7 ሚሊዮን እንደሆነ፤ ይህም ድንበር አልፈዉ ወደሌሎች ሀገራት የተሰደዱትን 15,4 ሚሊዮኖች እንደሚጨምር ገልጿል። ከተሰዳጆቹ አብዛኛዎቹ የሚስተናገዱት በድሃ ሀገራት እንደሆነም የተመድ ዘገባ አስተድቷል። በርሊን ላይ የቀረበዉ የስደተኞችን ሰቆቃ የሚያሳየዉ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያዉያን በስደት ሂደት የሚገጥማቸዉን ከአንደበታቸዉ አሰምቷል። ተሰዳጆቹ በአልጀሪያ አድገዉ ወደሞሮኮ ከዚያም ካናሪን ረግጠዉ ስፔን በስቃይ ሲደርሱ፤ ሌሎች በሊቢያ በረሃ ወደጣሊያን ለመግባት ላምፔዱዛ በጣር መድረሳቸዉን ይናገራሉ። የተረፉት ታሪክ ለመናገር ይብቁ እንጂ የነደደዉ የበረሃ አሸዋ ዉጦ ያስቀራቸዉ፤ ባህር ያሰጠማቸዉ፤ ሌላም አደጋ ህይወታቸዉን የቀማቸዉን ደግሞ ቤቱ ይቁጠራቸዉ። ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ከበርሊን ፊልሙን ተከታትሏል፤

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic