የዓለም የምግብ ቀንና ስጋት | ዓለም | DW | 17.10.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የዓለም የምግብ ቀንና ስጋት

በዓለም በምግብ ማጣትና እጥረት እየተቸገሩ የሚገኙ በርካታ ወገኖች ባሉበት በዚህ ወቅት የበለፀጉት አገራት እነሱን ለመርዳት ከመፋጠን ይልቅ ትኩረታቸዉ በባንኮች ላይ የተከሰተዉ የፋይናንስ ቀዉስ ላይ ሆኗል ሲሉ የቀድሞዉ የተመድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን ወቀሱ።

10,000 የሚሆኑ ህፃናት በድሃዎቹ አገራት የረባ ምግብ በማጣት ይሞታሉ

10,000 የሚሆኑ ህፃናት በድሃዎቹ አገራት የረባ ምግብ በማጣት ይሞታሉ

እሳቸዉ እንደሚሉት በሶስተኛዉ ዓለም አገራት 10,000 ህፃናት በዛሬዋ ዕለት ብቻ የተመጣጠነ ምግብ በማጣት ህይወታቸዉ ያልፋል። የዓለም የረሃብ ሁኔታን የሚያሳየዉ መዘርዝር በመኩሉ በዓለማችን ከሚገኙት አገራት 33ቱ በከፋ የርሃብ ችግር ላይ እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል።