ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በትግራይ ክልል አሁንም አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች በተለመደ ስራቸው ላይ ሳይሆኑ የተፈናቃዮች መጠልያ ጣብያዎች ሆነው እያገለገሉ ነው። በክልሉ ትምህርት ለማስጀመር በተደጋጋሚ ተደረጉ የተባሉ ጥረቶች እስካሁን አልሰመሩም
ለዓመታት ለመጠፋፋት የሚያደቡት የኤርትራና የሕወሃት ፖለቲከኞች ላጭር ጊዜም ቢሆን ከየሚጥሟቸዉ ወገኖች ጋር አበሩም አላበሩ በአማራና በኦሮሞ ልሒቃን መካከል የሚካሔደዉ ሽኩቻ «የአማራና የኦሮሞ ብልፅግና» በሚባሉት በገዢዉ ፓርቲ ቡድናት መካከል እንኳ በግልፅ እየታየ ነዉ።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ-መስተዳደር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት መሾማቸው የተገለጠው አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ የትግራይ ክልል ግዛታዊ አንድነትን ለማስጠበቅ እንደሚሠሩ ተናገሩ ። የተፈናቀሉ ያሏቸውን መልሶ ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ተግባራት እና ሌሎች ቀዳሚ አጀንዳዎችን እንደሚሠራባቸውም ዐስታውቀዋል ።
ለአካባቢ ተፈጥሮ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ከሀገራቸው አልፈው በዓለም መድረክ ከፍተኛ ተደማጭነትን ያተረፉት፤ ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷም።