ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠንቀቅ ኃይል በእንግሊዝኛ ምህፃሩ (EASF) የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 ቀን፣ 2013 ዓ.ም የሚደረገውን የኢትዮጵያ ምርጫ የሚከታተሉ 28 ታዛቢዎቹን ዛሬ በይፋ ወደ ሥራ አሰማራ። ኃይሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዐሥር አባል ሃገራት አሉት። ነገር ግን የሰኞውን ምርጫ የሚከታተሉ ታዛቢዎች የተውጣጡት ከስምንቱ ሃገራት ነው።
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ ለመወሰን ለሁለኛ ጊዜ ያደረገው ሙከራ ያለስምምነት ተበተነ። ምክር ቤቱ በአየርላንድ አቅራቢነት በትግራይ ክልል ግጭቱን ለማስቆም ጣልቃ መግባትን በሚጠይቀው ረቂቅ ላይ ህንድ ፣ ሩስያ እና በተለይም ቻይና በድጋሚ ተቃውመውታል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮችን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ አደረሱት የተባለዉ በደል «በሰብአዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል እና የጦር ወንጀል » ሊሆኑ ይችላሉ ሲል የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የበላይ አስታወቁ።
በጎ ፈቃደኛ የባህር ቃኚ የነብስ አድን ሰራተኞች በሜዴትራንያን ባህር በመስመጥ ላይ ከነበረች ጀልባ ከ100 በላይ ፍልሰተኞችን ታደጉ። ጀልባዋ ከተነሳችበት የሊቢያ የባሕር ዳርቻዎች ከ102 በላይ ሰዎችን አሳፍራ እንደነበር መቀመጫውን በርሊን ያደረገው « የባሕር ሰዎች 3» መርከብ የነብስ አድን ሰራተኞች ዛሬ አስታውቋል።