ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ባለፈው ቅዳሜ በታጣቂዎች በዘር ላይ ባነጣጠረው የጅምላ ግድያ የተጠቁና ከግድያው የተረፉ ተፈናቃዮች በከፋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት ተፈናቃይ እንዳሉት እስካሁን የመንግስት የፀጥታ ኃይሎችን ተከትሎ የሚደረግ የአስከሬን ለቀማ እና ቀብር የመፈጸም ስራ እና ቁስለኞችን የማሳከም ስራ እተከናወነ ነው፡፡
በናይል ውኃ አጠቃቀም የሦስትዮሽ ድርድር ዙሪያ የታዛቢነት ሚና ያለው የአውሮፓ ሕብረት የወንዙን የውኃ አጠቃቀም በተመለከተ ከሰሞኑ ለግብጽ ያደላ አቋም ማራመዱን ኢትዮጵያ አጣጣለች። ከሰሞኑ ውይይት ያደረጉት የአውሮፓ ሕብረት እና ግብጽ የናይል ውኃ አጠቃቀምን በተመለከተ ባወጡት የጋራ መግለጫ ለአንድ ወገን ያደላ አቋም ማራመዳቸው ታዉቋል።
ቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ አገሮች በሰላም ፣ በመልካም አስተዳደር እና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኞ እና ትናንት በአዲስ አበባ ያደረጉት ጉባኤ ለቀጣናው ተስፋን የሚያጭር መሆኑ ተነገረ። በመጀመሪያው የቻይና - አፍሪካ ቀንድ የሰላም ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጉባኤ ላይ ከኤርትራ በስተቀር ተሳትፈዋል።
የፈረንሳይ ፖለቲካ በአሁኑ ወቅት መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኑ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ለዚህም ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ እሁድ የተካሄደዉን የብሔራዊ ምክርቤት እና የሕግ አዉጭ አባላትን ምርጫ ተከትሎ በተገኘዉ ዉጤት ነዉ።