ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የጀርመን ፓርላማ «ቡንዴስታግ» በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት የናዚ ጭፍጨፋ ሰለቦችን አስቦ ዋለ። ፓርላማዉ በዛሬዉ እለት በናዚ ጀርመን በተለይ በአናሳ ፆታነታቸዉ ሰለባ የሆኑት ነዉ አስቦ የዋለዉ። ጀርመን እለቱን በይፋ ማሰብ የጀመረችዉ ከጎርጎረሳዉያኑ 1996 ዓ.ም ጀምሮ ነዉ። በእስራኤል እለቱ መታሰብ የጀመረዉ በጣም ቀደም ብሎ ነዉ።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የአፍሪቃ ሐገራትን ለመጎብኘት ዛሬ ኪንሻሳ-ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ገቡ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለአምስተኛ ጊዜ ወደ አፍሪቃ ጉዞ ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በተጨማሪ ደቡብ ሱዳንንም ይጎበኛሉ። አንድ መቶ ሚሊዮን ከሚገመተዉ የኮጎ ሕዝብ 40 በመቶዉ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነዉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ሁኔታ "በጣም የከፋ" ደረጃ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል አስታወቀ። ተቋሙ የመብት ጥበቃ ተቆርቃሪዎች ለእሥር እየተዳረጉ ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ቢሆንም ይህንን ለማስቀረት ጥረት እያደረግሁ ነው ሲልም አስታውቃል።