የዓለም ካቶሊክ ወጣቶች ቀን | ዓለም | DW | 29.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የዓለም ካቶሊክ ወጣቶች ቀን

የዘንድሮዉን የዓለም ካቶሊክ ወጣቶች ቀን ፖላንድ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። ከትናንት በስተያ አንስቶ ለቀጣይ አምስት ቀናት በሚዘልቀዉ በፖላንዷ ካራኮዉ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ የዓለም ካቶሊክ ወጣቶች ቀን ከአንድ መቶ በላይ ሃገራት የተዉጣጡ በርካታ ወጣቶች እየተሳተፉ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:51

የዓለም ካቶሊክ ወጣቶች ካራኮዉ ፖላንድ

«የሚምሩ የተባረኩ ናቸዉ፤ እነሱም ምህረትን ያገኛሉና፤» በሚል መሪ ቃል ለአምስት ቀናት በሚካሄደዉ በዓል ላይ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ተገኝተዋል። በዛሬዉ ዕለትም ፖላንድ ዉስጥ የሚገኘዉን ከ1,1 ሚሊየን የሚበልጡ አብዛኞቹም አይሁዳዉያን በናዚ ጀርመን ታጉረዉ የተገደሉበትን ኦሽዊትዝ የተባለዉን የማጎሪያ ስፍራ ጎብኝተዋል። ፖላንድ ዉስጥ ስለሚካሄደዉ የዓለም ካቶሊክ ወጣቶች ቀን አከባበር ዋርሶ የሚገኘዉን ስለሺ ይልማን በስልክ ጠይቄዋለሁ፤

ስለሺ ይልማ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic