የዓለም ኤኮኖሚ ግንኙነትና ኢትዮጵያ | ኤኮኖሚ | DW | 28.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የዓለም ኤኮኖሚ ግንኙነትና ኢትዮጵያ

የዓለም ኤኮኖሚ ግንኙነት ገጽታ በተለይ በወቅቱ የፊናንስ ቀውስ ሳቢያ ከሥር መሠረቱ መለወጥ ይዟል። በአንድ በኩል የአዳጊ አገሮች በንግድና በኤኮኖሚ መጠናከር በአንጻሩም የበለጸጉት መንግሥታት የመዳከም ሁኔታ የግንኙነቱን ገጽታ ከመቀየር ሌላ ምርጫ የሰጠ አይመስልም።

ረሃብ፤ የልማት ዕጦት ገጽታ

ረሃብ፤ የልማት ዕጦት ገጽታ

የቡድን-ሃያ መፈጠርና በተለይም ብሪክ በሚል አሕጽሮት የሚጠሩት አራት ሃገራት የብራዚል፣ የሩሢያ፣ የሕንድና የቻይና ሚና መጠናከር በዓለምአቀፉ የኤኮኖሚ ግንኙነትና በዓለም የምንዛሪ ተቋማት ውስጥም የሃይል አሰላለፍን እየቀየረ የሚሄድ ነው የሚመስለው። እነዚህ ሃገራት ዛሬ በዓለም ንግድ ላይ ሰፊ ድርሻ ሲኖራቸው በገንዘብ ክምችትም ቢሆን እጅግ ጠንካሮች ናቸው። እናም ወደፊት በዓለምአቀፉ ኤኮኖሚ የውሣኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ተጽዕኗቸው ማየሉ አይቀርም። ከሆነ ይህ ኢትዮጵያን ለመሳሰሉት የአፍሪቃ አገሮች የሚለውጠው ነገር አለ ወይ? በስኮትላንድ ዳንዲ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ንግድ ሕግ ባለሙያ ዶር/መላኩ ደስታ!

MM/AA