የዓለም ባንክ ዘገባና ኢትዮጵያ | ኤኮኖሚ | DW | 12.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የዓለም ባንክ ዘገባና ኢትዮጵያ

የዓለም ባንክ ሰሞኑን ባወጣው ዘገባው መንግሥታት በፖሊሲ  የተቃኘ ድጋፍ  ካላደረጉ  የዓለም የምጣኔ ሐብት እድገት እንደተጠበቀው አይኾንም ብሏል። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2018 ዓመታዊ የምጣኔ ሐብትን በላቀ ደረጃ ያስመዘግባሉ ከተባሉ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት መካከል ጋና በአንደኛነት ተጠቅሳለች፤ ኢትዮጵያ ትከተላታለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:15

የዓለም ባንክ የ2018 ዘገባ

የዓለም ባንክ ሰሞኑን ባወጣው ዘገባው መንግሥታት በፖሊሲ  የተቃኘ ድጋፍ  ካላደረጉ  የዓለም የምጣኔ ሐብት እድገት እንደተጠበቀው አይኾንም ብሏል። እንደ ዘገባው ከኾነ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2018 ዓመታዊ  የምጣኔ ሐብትን በላቀ ደረጃ ያስመዘግባሉ ከተባሉ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት መካከል ጋና በአንደኛነት ተጠቅሳለች፤ ኢትዮጵያ ትከተላታለች። ኢትዮጵያ አምና አንደኛ ተብላ ነበር። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት የምጣኔ ሐብቱን እድገት እንደሚጎዳ ደግሞ  አንድ ምሑር ገልጸዋል።  ዝርዝር ዘገባውን መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ።

መክብብ ሸዋ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic