የዓለም ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ኤኮኖሚ ሁኔታ | ኤኮኖሚ | DW | 06.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የዓለም ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ኤኮኖሚ ሁኔታ

የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት፣ አይ ኤም ኤፍ በዚህ ሳምንት ዋሽንግተን ውስጥ ከ187 ሀገራት የገንዘብ ሚንስትሮች ጋ ተገናኝተው ይመክራሉ።

ታዛቢዎች እንደሚገምቱት፣ ምክክሩ ዕድገት ባላሳየው የኤኮኖሚ ሁኔታ፣ ምዕራብ አፍሪቃን ያስጨነቀው የኤቦላ ወረርሽኝ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ጦርነቶች በኤኮኖሚው ላይ ባስከተሉት መዘዝ እና በመፍትሔው ሀሳብ ላይ ያተኩራል። ኤቦላ እና የዩክሬይን ውዝግብ በዓለም ኤኮኖሚ ላይ የደቀኑት ስጋት ቀላል አለመሆኑን የዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት፣ አይ ኤም ኤፍ ኃላፊ ክሪስቲን ላጋርድ አስጠንቅቀዋል።

ሮልፍ ቬንክል /ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic