የዓለም ቀይ መስቀልና አፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 20.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

   የዓለም ቀይ መስቀልና አፍሪቃ

ፕሬዝደንቱ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያወጀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አንስተዉ መነጋገራቸዉን አስታዉቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:14
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:14 ደቂቃ

የዓለም ቀይ መስቀልና አፍሪቃ

የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዝደንት ፔተር ማዉረር ትናንት በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያ እና የአፍሪቃ ሕብረት ባለሥልጣናትን አነጋግረዋል። ፕሬዝደንቱ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያወጀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አንስተዉ መነጋገራቸዉን አስታዉቀዋል። ከአፍሪቃ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉት ዉይይት የካምፓላ ሥምምነት የተባለዉን ዉል ገቢራዊ ለማድረግ ባጋጠሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸዉ ላይ ያተኮረ ነዉ። ኮሚቴዉ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል ያላቸዉን የመፍትሔ ሐሳቦች ያካተተ ሰነድም ለሕብረቱ ባለሥልጣናት ማስረከቡን ፕሬዝደንቱ አስታዉቀዋል። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ


 

Audios and videos on the topic