የዓለም ሙቀት መጨመርና ሰበቡ | ዓለም | DW | 27.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የዓለም ሙቀት መጨመርና ሰበቡ

ባለፉት 60 ዓመታት እየጨመረ ለመጣው የዓለማችን ሙቀት አብዩ ምክንያት ሰው ሰራሽ መሆኑን ዛሬ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት አስታወቀ ።

የተባበሩት መንግሥታት የዓየር ንብረት ለውጥ አጥኚዎች ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀው የዛሬ 6 ዓመት ባቀረበው ዘገባ ለዓለማችን ሙቀት መጨመር የሰው ልጅ ድርሻ 90 በመቶ ነው ሲል የዘገበውን አሁን ወደ 95 በመቶ ከፍ አድርጎታል ። ችግሩን ለመከላከልም መንግስታት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱና እጎአ እስከ 2015 አንድ የጋራ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ቡድኑ ጠይቋል ። ዛሬ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ይፋ የተደረገው ይኽው ዘገባ ባለ 2 ሺህ ገፅ ሲሆን ለፖሊሲ አውጭዎች የተዘጋጀ ተጨማሪ 36 ገፅ ማጠቃለያም አለው ። ዘገባው የተቀመረው በ 257 ሳይንቲስቶች ነው ። ስለዚሁ ዘገባ ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘውን ወኪላችንን ቴዎድሮስ ምህረቱን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ ጠይቄው ነበር ።

ቴዎድሮስ ምህረቱ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic