ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የሱዳን ሠራዊት አሁንም ከርቀት መድፍ እየተኮሰ እንደሆነ የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ አብራራው ተስፋ ተናግረዋል፡፡ አንድ የአካባቢው ነዋሪም የሱዳን ጦር ትንኮሳውን በአካባቢው ትናንት ማምሻውን ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያለማሰለስ የሚሰማው የጥቃት፣ የግጭት ጦርነት ዜና የኅብረተሰቡን የደህንነት እና ጸጥታ ይዞታ ስጋት ላይ እንደጣለው የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም። ለዚህም መፍትሄ ያመጣል በሚል የብዙሃኑ ዓይን እና ጆሮ በመንግሥት ይሁንታ በቅርቡ በተቋቋመው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ላይ አርፏል።
የትግራይ ባለሥልጣናት ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች ለቀናል ማለታቸዉን የፌዴራል መንግሥት አስተባብሏል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እንደተናገሩት "በተለያየ መልኩ ወደ ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ ፍለጋ የሄዱ፣ እና ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች ተቆጣጠራቸው በነበሩ አካባቢዎች የያዛቸው ናቸው " ብለዋል።
የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠንቀቅ ኃይል በእንግሊዝኛ ምህፃሩ (EASF) የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 ቀን፣ 2013 ዓ.ም የሚደረገውን የኢትዮጵያ ምርጫ የሚከታተሉ 28 ታዛቢዎቹን ዛሬ በይፋ ወደ ሥራ አሰማራ። ኃይሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዐሥር አባል ሃገራት አሉት። ነገር ግን የሰኞውን ምርጫ የሚከታተሉ ታዛቢዎች የተውጣጡት ከስምንቱ ሃገራት ነው።