የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ  | ኢትዮጵያ | DW | 16.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ 

የኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፌ ሉቱንዱላ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድርን ማስቀጠል በሚቻልበት መንገድ ላይ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር  መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሉቱንዳላ ወደ ሱዳንና ግብፅም ይሄዳሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:20

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ 


የወቅቱ የአፍሪቃ ኅብረት ሊቀመንበር የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፌ ሉቱንዱላ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድርን ማስቀጠል በሚቻልበት መንገድ ላይ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር  መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።ትናንት ኢትዮጵያ የመጡት ሉቱንዳላ ወደ ሱዳንና ግብፅም የሚጓዙ ሲሆን ሁለቱ አገራት ለመደራደር ፈቃደኞች ሲሆኑ ሂደቱ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል የሆኑት ካረን ባስ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገልጸው በምን ላይ እንደሚነጋገሩ ግን አላሳወቁም።ቃል አቀባዩ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያም ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።


ሰሎሞን ሙጬ
 ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ
 

Audios and videos on the topic