የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 10.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል መግለጫ

ሳዑዲ አረብያ ሰሞኑን ምሕረት ያደረገችላቸው ኢትዮጵያውያን የሕግ ታራሚዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሳዑዲ የረመዳንን ጾም ምክንያት በማድረግ ከለቀቃቸው ኢትዮጵያውያን መካከል ለረዥም ዓመታት እስራት የተፈረደባቸው ይገኙበታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:52

«ቀሪ ታራሚዎች የእስር ጊዜያቸው በሶስት አራተኛ ይቀነስላቸዋል»አቶ ነብያት

ቀሪ ታራሚዎችም የእስር ጊዜያቸው በሶስት አራተኛ ይቀነስላቸዋል ብለዋል። በዚሁ መግለጫ የኢትዮጵያ እና የአውሮጳ ሕብረት የቢዝነስ ፎረም ግንቦት 6 እና 7 በብራሰልስ ቤልጂየም እንደሚካሄድም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ አለው።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic