የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 06.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ

ከ94,4 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት በኢትዮጵያ ከፍተና የዋጋ ግሽበት እንዳለ መረጃዎች ያመለክታሉ። በሰኔ ወር 2009 ዓ/ም ያለዉ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በግንቦት ወር ከነበረዉ 8.7 በመቶ 0.1 በመቶ መጨመሩን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ያወጣዉ ዘገባ ይጠቁማል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10

የዋጋ ንረት

በዚህ ወር የአትክልትና የጥራጥሬ ዋጋ መቀነሱን ዘገባዉ ጠቅሶ፣ ግን የፍራፍሬ ዋጋ መጨመሩን ገልፀዋል። ለምሳሌ ባለፈዉ ወር ምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ ጭምሪ 12.3 በመቶ የነበረው፣በዚህ ወር ወደ 11.2 በመቶ መቀነሱ፣ በምግብ ነክ ያልሆኑት ላይ ሸቀጦች ጭማሪ ደግሞ ከ4.7 በመቶ ወደ 6.1 በመቶ ከፍ ማለቱ ዘገባዉ ጠቁመዋል።

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱን መሰረት አድርገን በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ምግብ ነክ የሆኑ ዉጤቶች በዕለት ተዕለት ኑሮዋቸዉ ላይ ምን ተፅዕኖ እንዳሳደረ አስተያየታቸዉን እንዲያጋሩን ጠይቀን ነበር። ከመካከላቸው በወሎ ዞን ደሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሙሃመድ አህመድ አንዱ ናቸው።

አቶ ገደፋዉ ይርሳዉ በምዕራብ ጎጃም መጫ አከባቢ የመንግስት ሠራተኛ መሆናቸዉን ተናግረው ደሞዝ ጭማር ከተደረገ በኋላ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዉጤቶች ዋጋ ጨምሯል  ይላሉ።

ስማቸዉን ሳይጠቅሱ በዋትስፓፕ ላይ የድምፅ መልዕክት የላኩልን የአፋር ክልል ነዋሪ ነኝ ያሉን ፣በአከባቢያቸዉ ስላለው የዋጋ ንረት ነግረውናል።

የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ ጌታቸዉ ተክለማርያም አገሪቱ ከዚህ በፊትት ካጋጠማት የዋጋ ግሽበት አሁን ያለዉ የዋጋ ግሽበት ያን ያህል አይደለም ስሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ለዋጋ ግሽበቱ መንስኤ ሊሆን የሚችለዉ በገበያዉ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠንና ገንዘቡ በገበያ ዉስጥ ሊገዛ የሚችለዉ እቃዎች አቅርቦት መጠን መሆኑን አንዱ መሆኑን ይናገራሉ። ድርቁም ለዋጋ ግሽበቱ አስተዋጽኦ አድርጓል ይላሉ።አሁን በኢትዮጵያ ያለዉን  ሁኔታም እንዲህ ይገልጻሉ።

በሀገሪቱ በመጠን የተሻለ የግብርና ምርት ቢኖርም አቅርቦት ላይ ክፍተት እንዳለ አቶ ጌታቸዉ ተናግረዋል።  የሀገሪቱ የግብርና ዘርፍ መዋቀራዊ ለዉጥ ማምጣት እንዳልቻለም አቶ ጌታቸዉ ገልጸዋል። የዋጋ ንረት የሀገሪቱ የገንዘብ ፖሊስ ዉጤት መሆኑን ተናግረው መፍትሄ ሊሆን ይችላል ያሉትን ተናግረዋል።

በዶይቼ ቬሌ ፌስቡክ ላይ የዋጋ ንረቱን በተመለከተ አስተያየት የላኩልን አሉ። አብርሃማን አል የተባሉ አስተያየት ሰጭ «ተጽዕኖውን ለምደነዋል! ያውም ከነ ማደናበሩ!» ሲሉ ፅፈዋል። ቃልቤሳ አርጋሚ የተባሉት ደግሞ «ያው እንደ ተለመደው ፆማችንን ያሳድረናል» ሲሉ ፅፈዋል። አያለዉ ኬር ገብረመስቀል የተሰኙት ደግሞ «ክብሪት እንኩዋን 1 ብር ከ50 ገብቷል! ያልጨመረ ነገር የለም! ምርር ብሎናል!» የምሉት አስተያየታቸዉን አጋርቶናል።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ 


 

Audios and videos on the topic