የዋጋ ንረትና መፍትሄው | ኢትዮጵያ | DW | 28.02.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዋጋ ንረትና መፍትሄው

የተፈላጊዎቹ ምርቶች ዋጋ ጭማሪ እጥፍና ከእጥፍ በላይ ነው። ነጋዴዎች፣ ከፍተኛው የዋጋ ጭማሪ ገበያ አሳጣን ሲሉ ያማርራሉ። የዋጋ ንረቱ በተለይ ዝቀተኛ ገቢ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል በእጅጎ ጎድቷል።የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን የተከተለው አዲሱ የትራንስፖርት ታሪፍ ችግሩን ማባባሱን የሚናገሩም አሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 31:41

የዋጋ ንረትና መፍትሄው

በኢትዮጵያ የሸቀጦችና የተለያዩ እቃዎች ዋጋ ከወራት ወዲህ እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ አሻቅቧል።ገደብ የለሹ ንረት ሸማቾችንም ነጋዴዎችንም አማሯል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ሸማቾች እንደሚሉት ያልጨመረ የምግብ ዋጋ የለም። የተፈላጊዎቹ ምርቶች ዋጋ ጭማሪ እጥፍና ከእጥፍ በላይ ነው። ነጋዴዎች፣ ከፍተኛው የዋጋ ጭማሪ ገበያ አሳጣን ሲሉ ያማርራሉ። የዋጋ ንረቱ በተለይ ዝቀተኛ ገቢ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል በእጅጎ ጎድቷል።የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን የተከተለው አዲሱ የትራንስፖርት ታሪፍ ችግሩን ማባባሱን የሚናገሩም አሉ።መንግስት ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ የኤኮኖሚ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን ቢናገርም የሸቀጦችን ዋጋ ከመናር ያስቆመው ነገር የለም።‘«የዋጋ ንረትና መፍትሄው|» የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው።በጉዳዩ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶች አሉን እነርሱም ዶክተር አጥናፉ ገብረ መስቀል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኤኮኖሚክስ መምህር ተመራማሪ ና የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ባለሞያዎች ማኅበር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል።አቶ ኦስማን ሸምሱ አምራችና ሸማቾችን የሚያገናኘው የፌደራል የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ እንዲሁም በኤኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለሚያተኩረው ካፒታል ጋዜጣ የሚሰራው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ወንድወሰን ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ ፦

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች