የወ/ሪት ብርትኳን ሚደቅሳ የይቅርታ ደብዳቤና እንድምታው | ኢትዮጵያ | DW | 18.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የወ/ሪት ብርትኳን ሚደቅሳ የይቅርታ ደብዳቤና እንድምታው

በእርግጥ በእድሜ ከወጣትነቱ ወደ ጎልማሳነቱ ሊሻገሩ ነው። ወደ ፖለቲካው የገቡት እንደሌሎቹ ቀደም ብለው ባይሆንም በዙም ደግሞ አልዘገዩም።

የወ/ሪት ብርትኳን ሚደቅሳ የይቅርታ ደብዳቤና እንድምታው

በእሳቸው ህይወት ውስጥ ህግ መነሻም መድረሻም፤ የሁሉ ነገር መቋጠሪያ ነው። ህግን አጥንተው ዳኛ ሆነዋል። ዳኛም ሆነው ችሎት ሰይመዋል። ፈርደዋል። ወስነዋል። ሁለት ጊዜ ለምርጫ ተወዳድረዋል። ሁለት ጊዜ ቃሊቲ ገብተዋል። ሁለት ጊዜ በምህረት ተለቀዋል። ለሦስተኛ ጊዜ በምርጫ ስላለመወዳደራቸው፤ ለሦስተኛ ጊዜም ቃሊቲ ስላለመውረዳቸው በእርግጥ አሁን ላይ መናገርም፤ መወሰንም አይቻልም። ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ።

አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር። 642 ቀናት። በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ ሲጠየቁ የሚመልሱትን መነሻ አድርገው፤ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ ዳግም መፈታታቸው የማይሆን፤ የማይደረግ የመሰላቸው ጥቂቶች አይደሉም። የወ/ሪት ብርቱኳን ጉዳይ ያበቃ፤ በአራት ነጥብ የተዘጋ ነው እያሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተናገሩት በእርግጥ የኢትዮዽያ አዲሱ ምክር ቤት በተሰየመ ማግስት ሌላ መልክ መያዙ አልቀረም። አንዳንድ ወገኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተጋብዘው ስለወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ መፈታት ሲጠየቁ የመለሱትን ይዘው መንግስት በቅርቡ ወ/ሪቷን ሊፈታ እንደሚችል ገምተው፤ ጠርጥረው ነበር። በአዲሱ ምክር ቤት ምስረታ ላይ ይሆናል ብለው ግን አልጠበቁም።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic