የወጣት ኢትዮጵያውያን የፎቶ አውደ ርዕይ በኒው ዮርክ | ባህል | DW | 11.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የወጣት ኢትዮጵያውያን የፎቶ አውደ ርዕይ በኒው ዮርክ

ከትናንት ሐሙስ አንስቶ ለ 10 ቀናት የሚዘልቅ የፎቶ አውደ ርዕይ ዩናይትድ ስቴትስ- ኒው ዮርክ ከተማ ተከፍቷል። በዚህም አውደ ርዕይ ላይ የ11 ወጣት ኢትዮጵያውያን የፎቶ ስራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:03
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:03 ደቂቃ

አውደ እርይ

በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ ሐሙስ ዕለት ለዕይታ መቅረብ የጀመረው አውደ ርዕይ « PHOTOGRAPHY IN ETHIOPIA » ይሰኛል። በዚህ 10 ቀናት በሚቆይ አውደ ርዕይ ላይ የተለያዩ በ11 ወጣት ኢትዮጵያውያን የተነሱ ፎቶዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

በኒው ዮርኩ አውደ ርዕይ እንዲሳተፉ ከተመረጡ ፎቶ አንሺዎች መካከል ነፃነት ፍቃዱ አንዷ ናት። በዚህ አውደ ርዕይ እንዲካፈል እድል ያገኘው ሌላው ወጣት ደግሞ ግርማ በርታ ይባላል። ግርማ በግል ድርጅቴ ውስጥ ግራፊክ ዲዛይነር ስሆን በትርፍ ጊዜዬ ደግሞ ፎቶ አነሳለሁ ይላል። ፎቶ ማንሳት በራሱ ነው የተማረው።

ግርማ እና ነፃነት ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄዱ የተወሰኑ የፎቶ አውደ ርዕዮች ላይ ቢካፈሉም፤ ከሀገር ውጪ ስራቸው ሲቀርብ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። ነፃነት ፎቶ ማንሳት የጀመረችው ገና ተማሪ ሳለች ሲሆን ፤ ፎቶ ማንሳት ራሷን የምትገልፅበት እና መርሳት የማትፈልጋቸውን ነገሮች በፎቶ አቅፋ የምታስቀምጥበት መንገድ እንደነ ትገልፃለች። ነፃነት ፎቶ ማንሳት የጀመረችው፤ ያነሳቻቸውን ፎቶዎች ወዲያው ማየት በምትችልበት ዲጂታል በሚባለው ካሜራ ነው።

ነፃነት ሌላም ስራ አላት፤ይህም ስራዋ፤ ለምርምር ወደተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንድትጓዝ ያደርጋታል። ያኔም ካሜራዋ ሁሌ ከእጇ እንደማይጠፋ ነፃነት ነግራናለች። ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ግን የግድ ሩቅ ቦታ መሄድ እና ውድ ካሜራ መግዛት አይወስነውም ትላለች፤ ሌሎች ፎቶ ማንሳት የሚወዱ ወጣቶችንን ስታበረታታ።የግርማ እይታ ደግሞ በብዛት የሚቀነጨበው በስልክ ካሜራው ነው።

እነዚህ ፎቶ አንሺዎች በኒው ዮርኩ አውደ ርዕይ እንዲሳተፉ ትልቅ ሚና የተጫወቱት፤ ወይዘሮ አይዳ ሙሉነህ ይባላሉ። ወይዘሮ አይዳ ራሳቸው ፎቶ አንሺ እና «ደስታ ፎር አፍሪቃ» የተሰኘ ድርጅት ባለቤት እንዲሁም በዚህ ድርጅት የፎቶ አነሳስ መምህር ናቸው። የአውደ ርዕዩ አላማ ምን እንደሆነ ገልፀውልናል።

ሁሉንም በድምፅ ያገኛሉ።

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic