የወጣቱ ኢትዮጵያዊ የደቡብ አፍሪቃ ተሞክሮ  | ወጣቶች | DW | 25.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ወጣቶች

የወጣቱ ኢትዮጵያዊ የደቡብ አፍሪቃ ተሞክሮ 

ኮስሞስ ገብረሚካኤል ይባላል። ባለፉት ዓመታት ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከተሰደዱት በርካታ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች መካከል አንዱ ነዉ። ነዋሪነቱን በደቡብ አፍሪቃ ደርባን ክዋዙሉ ናታል ከተማ ያደረገዉ ወጣት ኮስሞስ ገብረሚካኤል በዚያዉ በሚኖርበት ክዋዙሉ ናታል ክልል ዉስጥ በሚገኝ ፍትህ ቢሮ ለኢትዮጵያዉያን በማስተርጎም ሥራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:16

በኢትዮጵያ ለዉጥ ከመጣ ጀምሮ ሁኔታዉ ተሻሽሎአል

ኮስሞስ ገብረሚካኤል ይባላል። ባለፉት ዓመታት ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከተሰደዱት በርካታ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች መካከል አንዱ ነዉ። ነዋሪነቱን በደቡብ አፍሪቃ ደርባን ክዋዙሉ ናታል ከተማ ያደረገዉ ወጣት ኮስሞስ ገብረሚካኤል በዚያዉ በሚኖርበት ክዋዙሉ ናታል ክልል ዉስጥ በሚገኝ ፍትህ ቢሮ ለኢትዮጵያዉያን በማስተርጎም ሥራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።  ባለፉት ዓመታት በርካታ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች ወደ ደቡብ አፍሪቃ እየተሰደዱ መሆናቸዉ ፤ ብሎም ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመግባት በሚያቋርጡባቸዉ የተለያዩ ሃገራት እስር ቤት ዉስጥ መጣላቸዉ፤ ብሎም የአዉሪ ሲሳይ ሆኑ የሚል ዜና ተደጋጋሚ መሰማቶ የተለመደ ሆኖ ቆይቶአል። በደቡብ አፍሪቃ  ኢትዮጵያዉያን ትብብር ስለሌላቸዉ ኑሮ ቀላል አለመሆኑን የሚናገረዉ ኮስሞስ፤ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ከመጡ ወዲህ ግን ትንሽ መሻሻል እንደታየበት ገልፆአል።  
እንድያም ሆኖ ደቡብ አፍሪቃ በአብዛኛዉ ትምህርት ያልቀሰሙ ኢትዮጵያዉያን ተሰደዉ የሚመጡባትና ኑሮን መቆናጠጥ ያቻሉባት በመሆኗ ኢትዮጵያዉያን ከሚሰዱባቸዉ ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ደቡብ አፍሪቃ በአንጻራዊ ሃገር ገነት መሆንዋን ወጣት ኮስሞስ ተናግሮአል። በደቡብ አፍሪቃ ፍትህ ቢሮ ለኢትዮጵያዉያን በማስተርጎም ሥራ ላይ የሚገኘዉ ወጣት ኮስሞስ ገብረሚካኤል አነጋግረናል ፤ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ቃለ ምልልሱን ተከታተሉ። 


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ    

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች