የወይዘሪት ቡርቱካን ሚዴቅሳ መታሰር | ኢትዮጵያ | DW | 30.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የወይዘሪት ቡርቱካን ሚዴቅሳ መታሰር

ትናንት የታሰሩትን የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር ለማስለቀቅ የሚችለውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርግ ፓርቲው አስታወቀ ።

default

የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ምክትል የህዝብ ግንኙነት አቶ እንዳልካቸው ሞላ ዛሬ ለዶይቼቬለ እንደተናገሩት ትናንት ወይዘሪት ቡርቱካን ሚዴቅሳ ሲያዙ አብረዋቸው የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም እና ሾፌራቸውም እንግልትና ድብደባ ደርሶባቸዋል ። ወይዘሪት ቡርቱካን ለምን እንደታሰሩና ትናንት በፕሬፌሰር መስፍንና በሼፌሩ ላይ ደረሰ የተባለውን ዕንግልት ለማጣራት ከፖሊስ ኮሚሽንና ከፍትህ ሚኒስቴር ማብራሪያ ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም ።

ተዛማጅ ዘገባዎች