የወንዶች መገረዝ ህግ በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የወንዶች መገረዝ ህግ በጀርመን

የጀርመን ሚኒስትሮች ካቢኔ በሃይማኖት ላይ የተመሠረተዉ ወንዶች ልጆችን የማስገረዝ ባህልና ልማድ የሚያስቀጣ አይደለም ሲል ለወላጆች የመወሰን መብታቸዉን የሚፈቅድ ህግ አፀደቀ።

 ይህ አዲስ ህግ ብዙዎችን እዚህ ጀርመን እንዳስደሰተ የበርሊኑ ወኪላችን የላከልን ዘገባ ያስረዳል። በአንፃሩ የቆየዉ ህገመንግስት ላይ የሠፈረዉ የሰብዓዊ መብት ተሻረ ብለዉ ሌሎች ተነስተዋል። የማንም ሰዉ ሰብዓዊ መብቱና ክብሩ በሌላ ሰዉ መረገጥ፤ መደፈር፤ መነካትም የለበትም የሚለዉ የጀርመን ህገመንግስት መከበር አለበት ብለዉም አንዳንድ ሃኪሞች፤ የህግ ሰዎች የሸንጎ አባላትም ድምፃቸዉን በተደጋጋሚ አሰምተዋል። በሀገሪቱ ምክር ቤት ታይቶ ማለፍ የሚቀረዉ ይህን ህግ አስመልክቶ የተካሄደዉን ዉይይት የተከታተለዉ ይልማ ኃይለሚካኤል ዝርዝሩን ልኮልናል፤

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic