የወንድማማቾቹ የክስ ሒደት | ኢትዮጵያ | DW | 26.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የወንድማማቾቹ የክስ ሒደት

ኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን የቀድሞዉን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የበላይ ኃላፊ የጄኔራል ክንፈ ዳኘዉንና የቴሌ ኮሚኒኬሽን ባለሥልጣን የነበሩትን የታናሽ ወንድማቸዉን የአቶ ኢሳያስ ዳኘዉን የክስ ሒደት ዛሬ ተመልክቷል።

 
የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን የቀድሞዉን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የበላይ ኃላፊ የጄኔራል ክንፈ ዳኘዉንና የቴሌ ኮሚኒኬሽን ባለሥልጣን የነበሩትን የታናሽ ወንድማቸዉን የአቶ ኢሳያስ ዳኘዉን የክስ ሒደት ዛሬ ተመልክቷል። የፍርድ ቤቱ 15ኛ ወንጀል ችሎት በጄኔራል ክፍንፈ የክስ መቃወሚያ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ይዞት የነበረዉን ቀጠሮ ለሌላ ጊዜ አራዝሞታል። ፍርድ ቤቱ የአቶ ኢሳያስ ጠበቃን የክስ መቃወሚያ አድምጦ የአቃቤ ሕግን መልስ ለመስማት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

Audios and videos on the topic