የወባ ቀንና የአፍሪቃ አገሮች ጥረት | ጤና እና አካባቢ | DW | 25.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የወባ ቀንና የአፍሪቃ አገሮች ጥረት

ኢትዮጵያ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ይህን መድሃኒት መጠቀም ማቆሟን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ዲዲቲ መጠቀም እንዲቀር ለዉሳኔ ካደረሱ ምክንያቶች አንዱ የወባ ትንኝ መድሃኒቱን መቋቋም መጀመሯ ነዉ።


የአፍሪቃ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች የወባ ወረርሽኝ በተሻለ መልኩ ለመከላከል እየመከሩ ይገኛሉ። ህመሙን ለመከላከል  ዲዲቲን በርካታ ሀገሮች መጠቀም ማቆማቸዉን ቢገልፁም ደቡብ አፍሪቃ ዛሬም ጥቅም ላይ ማዋሏን እንደቀጠለች ተገልጿል። ኢትዮጵያ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ይህን መድሃኒት መጠቀም ማቆሟን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ዲዲቲ መጠቀም እንዲቀር ለዉሳኔ ካደረሱ ምክንያቶች አንዱ የወባ ትንኝ መድሃኒቱን መቋቋም መጀመሯ ነዉ።  
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለዉ-------በተያያዘ ዘገባ የወባ በሽታን ለማከም፣ ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት የተጀመሩ የተለያዩ መርሃግብሮችን የአዉሮጳ ኅብረትን ጨምሮ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና ሌሎች ሀገሮች ተሳትፏቿዉን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አስታወቁ። ዛሬ ታስቦ በዋለዉ ዓለም ዓቀፍ የወባ ቀን አስመልክቶች የአዉሮጳ ኅብረት የእድገት የምርምርና የጤና ኮሚሽነሮች ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ የወባ በሽታ በሚያጠቃቸዉ ሀገሮች የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም የወባ መከላከያም ሆነ ህክምና እንደማያገኙ ገልፀዋል። በወባ በሽታ በዓመት ስድስት መቶ ስልሳ ሺህ ሰዎች እንደሚሞቱ፤ ከእነዚህ ዉስጥም ዘጠና በመቶዉ አፍሪቃዉያን እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከሟቾች አብዛኞቹ ከአምስት ዓመት በታች ህፃናት መሆናቸዉ ችግሩን አሳሳቢና አጣዳፊ እንደሚያደርገዉ አመልክተዋል።የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል፤

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ገበያዉ ንጉሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች