የወሳኝ ኩነቶች ምዝግባ ተግባራዊነት | ኢትዮጵያ | DW | 04.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የወሳኝ ኩነቶች ምዝግባ ተግባራዊነት

የወሳኝ ኩነቶች ማለትም የልደት የሞት የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባዎች ከነገ ሐምሌ 30 ፣2008 ዓም ጀምሮ በይፋ ይጀመራል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:57

የልደት ማስረጃ

በኢትዮጵያ ወሳኝ ኩነቶች እንደተከሰቱ ህብረተሰቡ ለኢትዮጵያ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ እንዲያስመዘግብ ጥሬ ቀረበ ። ዛሬ በአዲስ አበባ በሂልተን ሆቴል በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ባሰሙት ንግግር የወሳኝ ኩነቶች ማለትም የልደት የሞት የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባዎች ከነገ ሐምሌ 30 ፣2008 ዓም ጀምሮ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀው ህብረተሰቡም ኩነቶቹን በማስመዝገብ የበኩሉን ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ።በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ከፕሬዝዳንቱ ሌላ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተጠሪዎችም ተገኝተዋል ። ስነስርዓቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic