የወልቃይት አቤቱታ | ኢትዮጵያ | DW | 23.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የወልቃይት አቤቱታ

የወልቃይት ህዝብ ላነሳዉ የማንነት ጥያቄ በሀገሪቱ ህገ መንግሥት መሠረት ምላሽ ለማግኘት እንደሚንቀሳቀስ የሚገልፀዉ አስተባባሪ ኮሚቴ ህዝቡ ያቀረበዉን ፍትሀዊ ጥያቄ የአካባቢዉ ባለስልጣናት ወደጎን ብለዉ ተፅዕኖ እያደረሱበት እንደሆነ ለዶቼ ቬለ ገለፁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:20
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:20 ደቂቃ

ወልቃይት

የህዝቡን ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ለማቅረብ ወደአዲስ አበባ መጓዛቸዉን የሚናገሩት የኮሚቴዉ አባላት ብዙ ተንገላተዉ መግባት ቢችሉም አቤታቸዉን ካቀረቡ በኋላ አሸባሪዎች ተብለዉ ተይዘዉ ለሰዓታት መመርመራቸዉንም ይናገራሉ።

ቀደም ሲል የወልቃይትን ህዝብ የአማራነት ጥያቄ ያነሱ ሰዎችም እስካሁን ያሉበት እንኳ አይታወቅም ይላሉ የአስተባባሪ ኮሚቴዉ አባላት።

Karte von Äthiopien

ከሁለት ሺህ ሰባት ወዲህም ሀገሪቱ ከራሷ አልፎ ለአፍሪቃ የሚበቃ ህገ መንግሥት እያላት የእኛ ጥያቄ በህገ መንግሥቱ ምላሽ ያገኛል በሚል ምሁራንንና ሀገሬዉን በማማከር ለህዋሃት ጽህፈት ቤት፤ ለአማራ ክልል፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት ጨምሮ ለሚመለከተዉ ሁሉ በሰነድ የተደገፈ አቤቱታቸዉን እንዳቀረቡም አስረድተዋል።

የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላቱ እንደሚሉት አሁንም ይህን ጥያቄ ያነሳሉ ያስተባብራሉ ተብለዉ የሚጠረጠሩ ሰዎች በአካባቢዉ ለወከባ ተዳርገዋል። ድብደባ የተፈጸመባቸዉ ግለሰብም ጎንደር ሃኪም ቤት እንደገቡም ጠቅሰዋል። መረጃዎቹን ለማጣራት ወደወልቃይት ዞን ባለስልጣናት ስልክ ብንደዉልም ስብሰባ ላይ ነን እና ሥራ ላይ ነን በሚሉ ምክንያቶች ለጥያቄያችን ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። የሀገሪቱ የፌደራል ጉዳዮች የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ወርቁ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ደረሰብን ስላሉት የእስር እንግልት እሳቸዉም ሆነ መሥሪያ ቤታቸዉ የሚያዉቀዉ ነገር የለም ካሉ በኋላ ያቀረቡት ጥያቄ ግን በሽምግልና እየታየ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች