የወላይታ መምህራን አቤቱታ | ኢትዮጵያ | DW | 24.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የወላይታ መምህራን አቤቱታ

በወላይታ ሶዶ የሚገኙ መምህራን ለቤት መስሪያ የተሰጣቸው መሬት እንደተወሰደባቸው አስታወቁ። ከእነሱ የተወሰደው መሬት ለሌሎች ተሰጥቷል ሲሉ ያማረሩት በ25 ማህበራት የታቀፉት እነኚህ መምህራን ናቸው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:10 ደቂቃ

መምህራን የቤት መስሪያ «መሬት ተወስዶብናል» ይላሉ

በደቡብ ክልል ወላይታ የሚገኙት መምህራን ለግንባታው ከሚያስፈልገው ወጪ 10 ከመቶ ቆጥበው የመሬት ካርታ አግኝተው የነበረ ቢሆንም መሬቱ በጥቅማ ጥቅም ለተሳሰሩ ለሌሎች እንዲሰጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡ የወላይታ ሶዶ ማዘጋጃ ቤት በበኩሉ “ይህን ድርጊት ፈጽሟል ያለውን መሀንዲስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና ለመምህራኑ ችግር መፍትሔ መስጠቱን ገልጿል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር የሚመለከታቸውን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል፡፡  

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር    
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic