የኮፐንሃገን ተስፋ የህዝብ አስተያየት | ዓለም | DW | 14.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኮፐንሃገን ተስፋ የህዝብ አስተያየት

በዴንማርክ ኮፐንሃገን ከተማ የአየር ንብረትን የተመለከተዉ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ከተጀመረ ዛሬ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል።

default

በዚህ ጉባኤ ላይ በርካታ ሃሳቦች እየተነሱ ብዙ ማነጋገር ይዘዋል። ሰላማዊ ሰልፎችም መካሄዳቸዉን ቀጥለዋል፤ በሳምንቱ ማሊለቂያም በሺ የሚቆጠሩ መታሰራቸዉ ተነግሯል። የአዉሮጳ ኅብረት ለአዳጊ አገራት ለቀጣይ ሶስት ዓመታት በየዓመቱ 2,4ቢሊዮን ዩሮ መመደቡን ባለፈዉ ዓርብ ይፋ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል። የአዉሮጳ የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎች ይህ ከቃል ያልዘዘለ ገንዘብ ከዚህ በፊት የተባለ አሁን ግን አረንጓዴ ቀለም ተቀብቶ የቀረበ ነዉ ብለዉታል። የብራስልሱ ወኪላችን ዘግቦበታል።

BdT Welt Tag des Wassers

በተጨማሪም በጉባኤዉ ላይ አፍሪቃን ወክለዉ ለድርድር የሚቀርቡት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ክፍለ ዓለሚቱ ከአየር ለዉጥ መዘዞች ጋ ተላምዳ ለመኖርም ሆነ ለዉጡን ለመግታት ለምታደርገዉ ጥረት ድጋፍ የሚሆን ገንዘብ፤ በአዳጊ አገሮቹ የተገመተ ማለት ነዉ፤ የምታገኝበትን መንገድ ሁሉ እንደሚሞክሩ ገልጸዋል። የሚታሰበዉ ዉጤት ካልተገኘ ደግሞ አፍሪቃ የሌሎችን ዉሳኔ አጃቢ እንደማትሆን ከወዲሁ አስታዉቀዋል፤ አልፎም ድርድሩን ረግጠዉ እንደሚወጡ አስጠንቅቀዋል። ዘገባዎቹን በተከታታይ ማድመጥ ይችላሉ።

ገበያው ንጉሴ

ሸዋዬ ለገሠ ፣ ሂሩት መለሰ