የኮካ ኮላ ምሥጢር ይታወቃልን? | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 09.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የኮካ ኮላ ምሥጢር ይታወቃልን?

በአብዛኛው የዓለም ክፍል ፤ ከከተማ እስከ ገጠር እጅግ መዛመቱ ይታወቃል። በኢንዱስትሪ ከሚመረቱ ለስላሳ መጠጦች ተብለው ከተመደቡት መካከል አንዱ ነው። ቡና ዓይነት ቀለም ያለው ፣ ጣፋጩና ፣ ሲቀዳ፣ ሿ! የሚለው «ለስላሳ» መጠጥ ፣

default

መመረት ከጀመረ ትናንት ልክ 126ኛ ዓመቱን ደፈነ ። ኮካ ኮላ!

አምራቹ ኩባንያ፣ በአሁኑ ጊዜ ከ 200 በሚበልጡ አገሮች፤ በቀን ፣ ከ 1,7 ቢሊዮን በላይ በጠርሙስም ሆነ ቆርቆሮ የተሞላ የኮካ ኮላ መጠጥ ያቀርባል። ፋብሪካውም ሆነ ኩባንያው፤ ዘንድሮ ፤ ካለፈው ጥር አንስቶ እስከ መጋቢት ማለቂያ ፤ በ 3 ወራት ብቻ 1,5 ቢሊዮን ዩውሮ ነው ትርፍ ያገኘው።

ኮካ ኮላን ኮካ ኮላ ያሰኘው ምንድን ነው? እውን የኮካ ኮላ አቀማመም ምሥጢር ይታወቃል? www.thisamericanlife.org የተባለ ድረ ገጽ፣ የጥንቱን፣ ዋናውን የ ኮካ ኮላ ጀማሪ የቅመማ ባለሙያ John Stith Pemberton (1831-1888)ያሠናዱትን የቅመማ መመሪያ አግኝቼአለሁ ሲል እ ጎ አ በ 1979 ዓ ም የተነሣ ፎቶግራፍ በቅርቡ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ በድረ ገጹ የሚታየው ፎቶግራፍ ፤ በአንድ መጽሐፍ በመሰለ ደብተር ገጽ 188 እና 189 ላይ የሠፈሩ የቅመማትን ዝርዝር ነው የሚያሳየው።

አምና ፣ የተቋቋመበትን 125 ዓመት በልዩ ሥነ ሥርዓት ያከበረው የመጠጥ ፋብሪካው ፣ ምርቱን ፣ ከምን ፣ ከምን እንደሚቀምመው በአብዛኛው ቢታወቅም፤ ተለይቶ የሚታወቅበትን ልዩ ጣዕም ጭምር የሚወስነው ወይም የሚወስኑትን ቅመማት ፣ ባለቤቶቹ በምሥጢርነት በዋናው ማዕከል በአትላንታ ጂዎርጂያ ዩናይትድ እስቴትስ ፤ በልዩ ካዝና ጠብቀዋቸው መኖራቸውም ሆነ ከትውልድ፣ ትውልድ ማስተላለፋቸው የታወቀ ነው ። አሁን፤ አሁን ፣አንዳንድ የሥነ-ቅመማ ተማራማሪዎች ምሥጢሩን ደርሰንባታል ባዮች ሆነዋል። ከምን ጭብጥ ነገር ተነስተው ነው ይህን የሚሉት? አብረን እንከታተል።

Flash-Galerie Coca Cola 125 Jahre

ኮካ ኮላ የብዙ ምሥጢራዊ ቅመማት ውጤት መሆኑ ነው የሚነገረው። በሬስቶራንቶች፤ የገበያ አዳራሾች፤ ኪዎስኮችና የቤንዚን ማደያ ጣቢያዎች የሚሸጠው ኮካ ኮላ፤

ጥንት «ኮፌኢን» የተሰኘው የተፈጥሮ ንጥረ ነገር በውስጡ ነበረበት ፤ ዛሬም በውስጡ ይገኝበታል።

ለነገሩ፤ ይኸው የጥንቱን ፤ ዋናውን መቀመሚያ ዘዴ አግኝቼአለሁ ባዩ ድረ ገጽ፣የ Everett Beal የቅመማ መመሪያ መጽሐፍ በሚል፣ እ ጎ አ የካቲት 28 ,1979፣ በአትላንታ ጋዜጣና ህገ-መንግሥት ጋዜጣ ተገልጦ የነበረውን ገልብጦ አቅርቦታል። እ ጎ አ በ 1992 ዓ ም፣ ይፋ ከሆነው የ Pemberton ማስታወሻ የሠፈረውን ጎን ለጎን አሥፍሮታል።

የኮካ ፈሳሽ ተዋጽኦ = በዩናይትድ እስቴትስ የመድኀኒት ቤት መለኪያ ፣ 3 ድራምስ

*4«አውንስ» የፈሳሽ ተዋጽኦ፣ኮኮ

የጣፋጭም ሆነ ጎምዛዥ ፍሬ ኮምጣጤ= 3 «አውንስ» * 3 «አውንስ»

ካፌኢን፣ = አንድ «አውንስ» * 1 «አውንስ» ሲትሬት ካፌይን

ስኳር፣ = 30 ፓውንድ ወይም 15 ኪሎግራም ገደማ * 30 ፓውንድ

ውሃ ፣ = 2,5 «ጋለን» * 2,5 «ጋለን»

ጭማቂ፣ = 2 Pint(1qrt) * 1 qrt

ቫኒላ ፣ = 1 «አውንስ» * 1 oz

ካራሜል፤ = 1,5 «አውንስ» ወይም ተጨማሪ ቀለም፣ * ቀለም ፣ በቂ

የማጣፈጫውን ቅመምም ሆነ የመጠጡን መለያ ጣዕም በመወሰኑ ረገድ፣መጠናቸው ይለያይ እንጂ፣ አልኮል፤ የብርቱካን ዘይት ፣ የሎሚ ዘይት ፤ የኑግ ዘይት፣ የኮረሪማ ዘይት ፤ የቀረፋ ዘይት የመሳሰሉት በ ፔምበርተን ሰነድም ሆነ በቢል ማስታወሻ መጠቀሳቸው አልቀረም።

ኮካ ኮላ ፣ ከሎሚ ከብርቱካንና ከመሳሰሉ ፍራፍሬዎች የሚቀመሙ የተለያየ ለስላሳ መጠጦች ቢኖሩትም ፣ የዋናው ኮካ ኮላ ጣዕም እንዳስገረመ አለ።

በበርሊን ከተማ ፕሮፌሰር Jürgen Gallinat የተባሉ የነርብ ሀኪም 15 ሰዎች ያደረጉት የኮካ ኮላን መለያ ዓርማ እንዲያዩ ካደረጉ በኋላ፣ ዘንግ በመሰለ ቀጭን ቧንቧ (Magnetresonanztomographie (MRT,MR) የተለያየ የኮላ «ሊሞኔድ» እንዲቀምሱ ያደረጋሉ። ሰዎቹ ንቃት እንደተሰማቸው ዶክተሩ ይገነዘባሉ። ነገር ግን ይህ የሆነው በመጠጣት እንዳልነበረ ነው የተመለከተው። «ኮላ የደስታ ስሜትን ይፈጥራል » የሚሉት፤ ኮካ ኮላ በሰዎች ላይ ስለሚያሳድረው ተጽእኖ ፤ በተባባሪነት በጀርመን ቴሌብዥን አንድ ፊልም የሠሩት ሚኻኢል ግሪትዝ ፤ «ማስታወቂያው ብቻ ፣ ዓርማው ፣ በሰዎች ዘንድ አዎንታዊ ስሜት መፍጠሩ የሚያስገርም ነው» ይላሉ።

ጣዕምን በተመለከተ---

መሠረታውያኑ የኮካ ኮላ ቅመሞች ይታወቁ እንጂ፤ ሁሉንም ተዋጽዖዎች በትክክል የሚያውቀው ራሱ ኩባንያው ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ምስጢር ነው። ሚኻኢል ግሪትዝ፣ 126 ዓመታት ሙሉ ምሥጢሩ ተጠብቆ ሊኖር አይችልም የሚል አስተሳሰብ ነበረን። ለፊልሙ ሥራ የተፈለጉ ተማሪዎች፤ በመጠጥ ሥነ- ቴክኒክ ነክ ቤተ ሙከራ 12 ጊዜ አስመስለው ለመቀመም ሞክረው ነበር፤ አልተሳካላቸውም።

ለሙከራ የተመረጡ 100 ሰዎች፤ 5 የኮካ ኮላ ዓይነቶች ቀርበውላቸው ነበር። ከእነዚህም መካከል በቤተ-ሙከራ የተቀመመው ሊሞኔድ አብሮ ቀርቦላቸው ነበረ። 44 ሰዎች፣ የኮካ ኮላ ጣዕም የሌለውን ለዩ።

ስኳር--

በእያንዳንዱ ሊትር ኮካ ኮላ 106 ግራም ስኳር አለ። ይህም መጠኑ ከ35 የስኳር እንክብል ጋር የሚስተካከል ነው።

ውሃ---

ለአንድ ሊትር ኮካ ኮላ፣ በፋብሪካው 2 ሊትር ውሃ ነው የሚያስፈልገው። በየዕለቱ በዓለም ዙሪያ ለሚጠጣው 307 ሚዮን ሊትር ኮካ ኮላ ቅመም 614 ሚሊዮን ሊትር ውሃ ያስፈልጋል። በህንድ አገር፤ አርሶ አደሮች ኮካ ኮላ፣ ለማሳችን የሚያስፈልገንን ውሃ ተሻማብን በማለት ቅሬታ ማሰማታቸው ተመልክቷል።ማያካኢል ግሪትዝ እንደሚሉት፤ ኮላካ ኮላ ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ ለማስታወቂያ 11 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርጓል። በያመቱ ውሃ ለማግኘትና ለሌሎች የማኅበራዊ ፕሮጀክቶች ግን ፣ 50 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የሚያወጣው።
ሱስ አስያዝ ዕፅ ---

ቀደም ባለው ዘመን ፤ ኮካ ኮላ የኮኬይን ጠብታ ሳይኖረው እንዳልቀረ ይገመት ነበር። ኮካ ኮላ ለማንኛውም፤ ይህ መሠረቢስ ወሬ ነው ሲል እስካ ዛሬ ድርስ በጥብቅ ነው የሚያስተባብለው። ከዚህ ሌላ፤ 100 ሚሊ-ሊትር ኮካ ኮላ 10 ሚሊ ግራም ኮፌኢን አለው። በተመሳሳይ መጠን ቡና 60 ሚሊ ግራም ኮፌኢን ነው ያለው። በዓለም ውስጥ ፣ ኮካ ኮላ የማይገኝባቸው አገሮች፤ ሰሜን ኮሪያ፤ በርማና ኩባ ናቸው። የጀርመን ቴሌቭዥን ከትናንት በስቲያ ስለ ኮካ ኮላ ያቀረበውን ፊልም ዕድሜው በ 14 እና 49 ዓመት መካከል ያለ፤ 1,55 ሚሊዮን ህዝብ ተመልክቶታል። 12,9 ከመቶ ወጣቶች ሲሆኑ ፣ ጎልማሶች ደግሞ 10,7 ከመቶ ብቻ ነበሩ። ኮካ ኮላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጀርመን የገባው እ ጎ አ በ 1929 ዓ ም ነው።

An undated picture shows Coca-Cola Santa Claus artwork of artist Haddon Sundblom. According to the legend, on May 8, 1886 the pharmacist John Pemberton invented the recipe for Coca-Cola, 6 May 2011. Photo: The Coca Cola Company/dpa/HO/FOR EDITORIAL USE ONLY / NO SALES

እ ጎ አ ግንቦት 8 ቀን 1886 ዓ ም፣ በአትላንታ ፤ ጆርጂያ ፤ ዩናይትድ እስቴትስ ፣ ለራስ ምታት መድኀኒት ይሆናል ብሎ መድኀኒት ቀማሚው ፣ ጆን ኤስ ፔምበርተን ከ ኮኮዋ ቅጠልና ፍሬ ቀምሞ በሶዳ ውሃ በጥብጦ ያዘጋጀው ኮካ ኮላ የተባለው መጠጥ፣ ድካምንና ራስ ምታትን እንዲሁም ድብርትን እንዲያስወግድ ፣ በተጨማሪም የተባእታይ ወሲባዊ ስሜትን እንዲያነቃቃ ነበረ የታለመው። ጀማሪው ፔምበርተን ፤ በዚህ አልከሰበም። ከመሞቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ፣ አሳ ካንደለር ለተባለ ሰው የቅመማ ውጤቱን በ 2,300 ዶላር ሸጠለት። ካንድለር፤ ኮላካ ኮላን ፣ የአሜሪካ «ብሔራዊ መጠጥ» እንዲባል ሳያበቃ እንዳልቀረ ነው የሚነገርለት።

Logo des Getränkeherstellers Coca Cola

«ኮካ ኮላ » በሚል ርእስ መጽሐፍ የጻፈችው ጀርመናዊቷ ደራሲ አንድሪያ ኤክስለር፣ በምዕራቡ ዓለም ፣የተንዠረገገ ነጭ ጺም፣ ያለው ቀይና ነጭ ቀለም ያለው ወፍራም ረጅም ጥበቆ መሳይ ለብሶ የሚታየው «ሳንታ ክላውስ »፣ «ቫይናኽትስማን» (የገና ሰው እንደማለት ነው ፣)

እናም ይህን የገና ሥጦታ አዳይ ፣ በራሱ የማስታወቂያ የፈጠራ ችሎታ እ ጎ አ በ 1931 ያስተዋወቀው ኮካ ኮላ መሆኑን በመጥቀስ እንዲህ ትላለች።

7,«ኮካ ኮላ በእርግጥ ይህን ሳንታ ክላውስን በራሱ በኩባንያው የታወቁ ቀለሞች ቀይና ነጭ ቀለማት ያሸበረቀ ልብስ አልብሶ ማሳየቱ፣ በዓለም ዙሪያ ወዲያው ነው ተቀባይነትን ያስገኘለት። እዚህ ላይ የሚያሳየው፤ ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን ኮካ ኮላ ለገበያ የረቀቀ የማስተዋወቅ ችሎታ እንደነበረው ነው።»

በበርሊን የኮካ ኮላ ቃል አቀባይ Geert Harzmann፤ ስለ ለስላሳ መጠጡ አዘጋጃጀት እንዲህ ይላሉ---

10,«ኮካ ኮላ የትም ቦታ በማይለወጥ የራሱ በሆኑ የቅመማ ውጤቶች ነው የሚዘጋጀው። ዋናው ለዚህ የሚያስፈልገው ውሃም ቢሆን፤ የተፈጥሮ ንፁህ የሚጠጣ ውሃ ሲሆን በየአካባቢው የሚገኘው ነው ለዚህ ዓላማ የሚውለው። እርግጥ የኩባንያውን ደረጃ በሚጠብቅ በልዩ መልክ ነው የሚዘጋጀው።»

ጥም እንዲቆርጥ የተዘጋጀው ለስላሳ መጠጥ ፣ በአሁኑ ዘመን መላውን ዓለም እንዳጥለቀለቀ የሚገኝ መሆኑ የታወቀ ነው። ድንበርም ሆነ ርዕዮትም አልገታውም።

ኮካ ኮላ በቻይናም ገበያ ፍለጋ ዘልቆ ከገባ ከ 30 ዓመታ በላይ ሆኖታል።

ቻይናዊው የዶቸ ቨለ ጋዜጠኛ ዳይ ዪንግ---

2,«ትንሽ ልጅ በነበርኩበት ጊዜ ይ ህ መጠጥ አስደናቂ ሆኖ ነበረ የሚታየኝ። አንድም ጊዜ አንድ የኮካ ኮላ ጠርሙስ ይዤም ሆነ ጠጥቼ ባላውቅም! ይሁንና ስሙ ራሱ ያማልለኝ ነበር። ኮካ ኮላ ማለት በቻይንኛ፤ «ይጣፍጣል ደስታም ይፈጥራል» የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠው።»

እንደ ዘመኑ የህክምና ሳይንስና የሥነ ቴክኒክ እመርታ፣ ኮካ ኮላም ፣ በለስላሳ መጠጡ ቅመም የሚገኙ ተዋጽዖዎች ለጤንነት ጠንቅ እንዳይሆኑ ፣ የስኳር መጠን እንዲቀነስ እያደረገ ማዘጋጀት ከጀመረ ቆየት ማለቱ ይነገራል።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 09.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14sTH
 • ቀን 09.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14sTH