የኮንጎው ውጊያ | አፍሪቃ | DW | 28.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኮንጎው ውጊያ

የኮንጎን ጦር ለማገዝ የተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጣልቃ ገብ ኃይል በኮንጎ አማፂ ቡድን M23 ላይ ኃ ዛሬ በሄሊኮፕተሮች ጥቃት ማድረሱ ተዘግቧል ። አማፂው ቡድንም የኮንጎ ጦርና የተመድ ኃይሎች የአየር ጥቃት እንደሰነዘሩበት አሰታውቋል ።


እንደገና ያገረሸው የኮንጎ ጦር ና M 23 የተባለው አማፂ ቡድን ውጊያ አንድ ሳምንት ሊሞላው ነው ። ውጊያው ዛሬም ቀጥሎ 3 ሺህ ጠንካራ ወታደሮች ያሰለፈው የተባበሩት መንግሥታት የኮንጎ ጣልቃ ገብ ኃይል ዛሬ በሄሊኮፕተሮችንና በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት በመሰንዘር ለኮንጎ ጦር ድጋፍ ሰጥቷል ። M 23 ም ጥቃት እንደተፈፀመበት አረጋግጧል ። የጣልቃ ገቡ ኃይል ቃል አቀባይ ሌተና ኮሎኔል ፌሊክስ ባሴ እንደተናገሩት ጥቃቱ የተፈፀመው ከጎማ ውጣ ብሎ በሚገኘው ኪባቲ በተባለው ኮረብታ ላይ ነው ። ይህን መሰሉ የጣልቃ ገቡ ጦር እርምጃ ግን ለኮንጎ ችግር በተናጠል መፍትሄ ማምጣቱ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት አጠራጣሪ ነው ።

Unruhen Kongo Goma

አካል ጉዳተኞች በጎማ

በእንግሊዘኛው ምህፃር ISS የተባለው የፀጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ ዴቪድ ዙሜኑ ይህን ከሚሉት አንዱ ናቸው ።« ዓለም ዓቀፉ ኃይል ብቻውን ችግሩን ያቃልላል ብሎ ማመን ስህተት ነው ። ችግሮቹ በአገሪቱ አጠቃላይ መዋቅሮች ውስጥ ስር የሰደዱ ናቸው ። ይህ ደግሞ መፍትሄ ሊያገኝ ይገባል ። ባለፈው የካቲት በአካባቢው ሃገራት የተፈረመው የሰላም ስምምነት የዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ችግር መጠነ ሰፊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ። ችግሩን የመፍታት ሃላፊነቱንም ለመንግሥትና ለሌሎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዘርፎች አከፋፍሏል ። ስምምነቱ የኪንሻሳ ባለሥልጣናት የምር የፖለቲካ ተሃድሶ እንዲያካሂዱም ጠይቋል ። »

ARCHIV Treffen afrikanischer Staatschefs in Uganda QUALITÄT

ካቢላና ካጋሜ


ባለፈው ዓመት ጎማን ለአጭር ጊዜ የተቆጣጠረው አማፂው M23 ወደ ሰሜን የሃገሪቱ ክፍል ቢያፈገፍግም ጎማና አካባቢዋን ማጥቃቱን አላቆመም ። ምንም እንኳን M 23 ጥቃት መሰንዘሩን ቢቀጥልም ቡድኑ ግን በመዳከም ላይ ነው ይላሉ ዴቪድ ዙሜኑ

«M23 አሁን ወደ መዳከሙ መሆኑን መገንዘብ አለብን ። እንደሚመስለኝ አመራሩ ወደ መበታተኑ ተቃርቧል ። የተመድ የአጥኚዎች ቡድን እንዳወጣው ዘገባ ከሆነ ከውጭ ማለትም ከጎረቤት አገራት የሚያገኙት ድጋፍ እየቀነሰ ነው ። እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ተደማምረው ቡድኑ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አድርገውታል ። »በዚህ የተነሳም ይላሉ ዙማኔ ቡድኑ የቀረው አማራጭ ወይ መንግሥትና ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በጀመሩት ጥረት ለመደራደር መዘጋጀት ና መሣሪያቸውን አስረክበውም ከጦሩ ጋር መቀላቀልን መቀበል አለያም የሚጠብቀው የተባበሩት መንግሥታት ጣልቃ ገብ ኃይልና የኮንጎ ጦር የሚሰነዝሩት የተባበረ ጥቃት ይሆናል ። ራድዮ ኦካፒ የተባለው የኮንጎ ራድዮ ጣቢያ እንደዘገበው M23 ትናንት ከምስራቃዊቷ ከተማ ጎማ 20 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ በኮንጎ ጦር ላይ ጥቃት

Kongo Rebellen im Hauptquartier Lubumbashi

የኮንጎ አማፅያን

ሰንዝሯል ። በአሶስየትድ ፕሬስ ዘገባ መሠረት ከዚያ ቀደም ሲል አማፂው ቡድን በሰነዘራቸው ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ። የጎማ አካባቢ ነዋሪዎች በዚያ የተሰማራው የተመድ ኃይል በቂ ጥበቃ አላደረገልንም ሲሉ ባለፈው ቅዳሜ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል ። ዴቪድ ዙሜኑ ዓለም ዓቀፉ ሰላም አስከባሪ ኃይል የቀድሞውን ዝናውን ማስመለስ አለበት ይላሉ

KIKWETE Portrait_face.jpg Tansania, Dar Es Salaam, 2005 Aufnahme: Badra Masoud Präsidentschaftskandidat der Regierungspartei CCM, Jakaya Kikwete, bei einer Wahlkampfveranstaltung zu Parlaments. und Präsidentschaftswahl in Tansania am 30. Oktober 2005 Uebertragung der Rechte dieses Bildes an DW-Online Original Message From: badra masoud To: Sent: Wednesday, September 28, 2005 2:10 PM Subject: Re-Tanzania Campaign Pictures Att: Maya Refer to our conversation I will be sending some pictures as much as I can. All these pictures was taken by DW correspondent Badra Masoud in Dar es Salaam, Tanzania are legally to be used by DW.

ጃካያ ኪክዌቴ

«የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃይሎች በዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ምንም የጥቅም አላስገኙም ። እንዲያውም አሁን ምንም ዓይነት ጥበቃ አላደረገልንም በሚሉ ነዋሪዎችና በተመድ ኃይሎች መካከል ውጥረት ተፈጥሯል ።

ስለዚህ አሁን የተመድ የቀድሞ ተዓማኒነቱ እንዲመለስና በዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ የሰላም ተልዕኮው ለሰማዊ ሰዎች ጥበቃ ማድረግና በM23 ስር የተሰለፉትን አማፅያን ማሸነፍ እንዲችል አንድ ነገር መደረግ አለበት ። »
የኮንጎው ውጊያ ለአካባቢው ሃገራትም ሰላም አልሰጠም ። ለምሳሌ ታንዛኒያ ከምስራቃዊቷ የኮንጎ ግዛት ኪቪ በሚጎርፉ ስደተኞች እየተጥለቀለቀች ነው ። በመሆኑም፣ ታንዛኒያ በኮንጎ በተሰማራው በዓለም ዓቀፉ ኃይል ሥር ወታደሮቿን አሳልፋለች ። የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጃካያ ኪክዌቴ የሩዋንዳውን ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን ግጭቱን በማባሳስ ይከሳሉ ። ኪክዌቴ ባለፈው ግንቦት በተካሄደው የአፍሪቃ ህብረት ጉባኤ ላይ ካጋሜ የኮንጎው መሪ ጆሴፍ ካቢላና የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ከሚወጓቸው አማፂያን ጋር እንዲነጋገሩም ሃሳብ ማቅረባቸው ውጥረቱን አባብሶታል ። ከዚህም በኋላ ኪክዌቴና ካጋሜ የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል ።
i

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic