የኮንሶና የአሌ ጎሳን በማጋጨት የተጠረጠሩ ታሠሩ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 22 2013ማስታወቂያ
የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የኮንሶና የአሌ ማኅበረሰብ አባላትን አጋጭተዋል፣ የሰዉ ሕይወትና ንብረት አጥፍተዋል ብሎ የጠረጠራቸዉን 310 ሰዎች አሰረ። የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ ዛሬ ለዶቼ ቬለ (DW) እንዳሉት ቢሮው ሰሞኑን ባካሄደው ዘመቻ ካሰራቸዉ ተጠርጣሪዎች ዉስጥ ባለ ሥልጣናት፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ገበሬዎች ይገኙበታል። ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሁለቱ ማህበረሰብ አባላት መካከል ደም ሲያፋስስ የቆየው ግጭት ባለፈው እሁድ ባህላዊ የእርቅ ስረዓት ከተደረገ በኋላ የአካባቢው ሰላም እየተሻሻለ ነዉ። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የኮንሶና የአሌ ብሄር ባህላዊ ንጉሦችና የአገር ሽማግሌዎች «ከእርቅ ስረዓቱ በኋላ የንግድ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፣ ለወራት ተቋርጠው የከረሙ ገበያዎችም መቆም ጀምረዋል» ብለዋል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ