የኮቪድ-19 ሦስተኛ ማዕበል በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 23.08.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኮቪድ-19 ሦስተኛ ማዕበል በአዲስ አበባ

አዲስ አበባ በሶስተኛው የኮቪድ-19 ማዕበል ውስጥ ትገኛለች ተብሎ እንደሚታመን የከተማው የጤና ቢሮ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ካለፉት አራት ሳምንታት ወዲህ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለጽኑ ሕመም የሚዳረጉ ግፋ ሲልም ሕይወታቸውን የሚያጡ አዲስ አበቤዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:25

የኮቪድ-19 ሦስተኛ ማዕበል በአዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ሶስተኛ ዙር የኮሮና ተዋሲ ስርጭት ማዕበል ክስተት ለመስተዋሉ አመላካች ቁጥራዊ ሁኔታዎች መታየታቸው ተገለጸ፡፡

በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ በተዋሲው ጦስ በፅኑ የሚታመሙ እና ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር ባለፉት አራት ሳምንታት ከጤና ተቋሟቱ አቅም በላይ ሆኖ ተስተውሏል ብሏል የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ፡፡

ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ያለው የተዋሲው ክትባት ቁጥር ከፍ እያለ በመሆኑ በቅርቡ ከአንድ ሚሊየን የላቁ ዜጎችን በመዲናዋ ብቻ ለመከተብ እቅድ መያዙን የገለጹት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ህብረተሰቡ ክትባቱን በየመንግስት ጤና ተቋማት በነጻ እንዲከተቡ አሳስበዋል፡፡

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የመዲናዋ ነዋሪዎች ግን ህብረተሰቡና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሁንም የላላ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic