የኮሮና ዳግም መስፋፋት ስጋት በአውሮጳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 31.08.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የኮሮና ዳግም መስፋፋት ስጋት በአውሮጳ

አውሮጳ ውስጥ የኮሮና ተሐዋሲ ወረርሽኝ ዳግም ቁጥሩ መጨመር አኅጉሪቱን አሳስቧል። ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከፍተኛ ሥርጭት ከታየባቸው የአውሮጳ ሃገራት መካከል የምሥራቅ አውሮጳ ሃገራት ቀዳሚውን ስፍራ ይወስዳሉ። ጆርጂያ፤ ንዑሷ ኮሶቮ እና ሞንቴኔግሮ ውስጥ ተሐዋሲው በከፍተኛ ፍጥነት እና ስፋት መሰራጨቱን ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:09

እስከ ታኅሣሥ 1 ድረስ  236 ሺ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ

አውሮጳ ውስጥ የኮሮና ተሐዋሲ ወረርሽኝ ዳግም ቁጥሩ መጨመር አኅጉሪቱን አሳስቧል። ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከፍተኛ ሥርጭት ከታየባቸው የአውሮጳ ሃገራት መካከል የምሥራቅ አውሮጳ ሃገራት ቀዳሚውን ስፍራ ይወስዳሉ። ጆርጂያ፤ ንዑሷ ኮሶቮ እና ሞንቴኔግሮ ውስጥ ተሐዋሲው በከፍተኛ ፍጥነት እና ስፋት መሰራጨቱን ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ብሪታንያ፣ ሩስያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ስፔንም ዳግም በተሐዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የጨመረባቸው ሃገራት ውስጥ ተመድበዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት ይፋ እንዳደረገው እስከ መጪው ኅዳር ወር መጨርሻ ወይም የታኅሣሥ ወር መጀመሪያ 236 ሺ ሰዎች በወረርሺኙ ሊሞቱ ይችላሉ ብሏል። 

የኮቪድ ወረርሺኝ በአውሮጳ ዳግም እየስፋፋ መሆኑን ያዓለም የጤና ድርጅት ትናንት ዐስታውቋል። በአለም ዙሪያ በኮቪድ ተሐዋሲ ወረርሺኝ ከሞቱት 4.5 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ 1.3 ሚሊዮኖቹ አውሮጳውያን መሆናቸው የሚታወቅ ሲህን፤ በአሁኑ ወቅትም ተሐዋሲው ዳግም እየተስፋፋ በመሆኑ ሌሎች በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሺኙ ሊሞቱ ይችላሉ እየተባለ ነው። 
 የአለም የጤና ድርጅት ያውሮጳ ዳይሬክተር  ዶክተር ሀንስ ክሉግ  ትናንት ኮፐን ሀገን ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳታወቁት ከሆነ፤  እስከ መጪው ህዳር ወር መጨርሻ ወይም የታህሳስ ወር መጅመሪያ ድረስ በአውሮፓ 236 ሺ ሰዎች በወረርሺኙ ሊሞቱ ይችላሉ። ድምጽ በበርክታ የአህጉሩ አገሮች የሆስፒታሎች መጨናነቅና የሚሞቱ ሰዎች ብዛትም እየታየ ነው። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ እስከሚቀጥለው ታህሳስ አንድ ድረስ  236 ሺ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ።

የአለም የጤና ድርጅት የአውሮፓው ክፍል ከ27ቱ የህብረት አገሮች በተጨማሪ፤ ሌሎች 26 የካውኮስና የባልካን አገሮችን የሚያጠቃልል ሲሆን፤ በሁሉም አገሮች፤ ይበልጥ ግን ኢኮኖሚያቸው አንስተኛ በሆኑትና ከህብረቱ ውጭ በሆኑት  አገሮች ተዋህሲ በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን ዶክተር ሃንስ አክለው ገልጸዋል። ለተዋሲው በፍጥነት መስራጨትና ለወረርሺኝ ዳግም መስፋፋት፤ በተለይ ዴልታ የተባለው የተዋህሲው ዝርያ በፍጥነት ተዛማች መሆኑና፤ በበርክታዎቹ አገሮችም ተዋሲው እውን መሆኑ ፤ ሁለተኛ የክትባቱ ሂደት መጓተቱ፤ ሶስተኛ የነበሩት እገዳዎችና ክልከላዎች መነሳታቸውና፤  በበጋው ወቅት የታየው የሰዎች ከፍተኛ ዝውውር አይነተኛዎቹ ምክኒያቶች እንደሆኑ ነው የሚነገረውና የሚታመነው።  

ወረርሺኙ በተለይ ክትባት በብዛት ባልተሰጠባቸውን ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ባሉት ያውሮፓ አገሮች አሳሳቢ መሆኑን የገለጹት ዶኦክተር ሃንስ፤ በሌሎችም ቢሆን ክትባትን ችላ የማለት ወይም ያለማመን አዝማሚያ መኖሩን አውስተው፤ ከዚህ አይነት አስተሳሰብ መላቀቅ አስፋላጊ  መሆኑን እና ክትባት መብትም ሀላፊነትም መሆኑን አስገንዝበዋል  ድምጽ መከተብ  መብት ብቻ ሳይሆን ሀላፊነትም ነው።  በአህጉሩ የክትባት ሂደት መጓትቱና ያንዳንዶች ለመክተብ ፈቃደኛ አለመሆን አሳስቢ ነው።  በተለይ በአሁኑ  በዙ የኮቪድ ክልከላዎች እየተነሱ ባሉበት ወቅት መከተብ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።  የተዋህሲውን መስፋፋት ለመግታት፤ የታማሚዎችን ቁጥር ለመቀንሳና በወረርሺኙ ምክኒያት የሚሚጣውን ሞት ለማስቀረት ክትብት  አስፈላጊና ወሳኝ ነው።  አዲሱ የተዋህሲው ዝርያ እንዳይስፋፋም ይረዳል።  ክትባትን መጠራጠርና ሳይንስን መካድ ከዚህ አደገኛ ወረርሺኝ እንዳንወጣ ከሚያደርገን በተቀር ምንም የሚያስገኘው ጥቅም የለም ብለዋል በመግለጫቸው። 

እስካሁን ከጠቅላላው የአውሮፓ ህዝብ ግማሹ ወይም አምሳ ከመቶ የሚሆኑት  ሙሉ የኮቪድ ክትባት የወሰዱ ቢሆንም፤ አሁን ግን የሚከተቡ ሰዎች ቁጠር እየቀነሰ እንደሆነ ነው የሚገለጸው። በተለይ ደሀ በሆኑት የአውሮፓ አገሮች ደግሞ የክትባት አቅርቦትና ስርጭት ችግር ያለ መሆኑን ተክትሎ፤ እስካሁን የህዝባቸውን 10 ከመቶ ባቻ እንዳስክተቡ ነው የሚታወቀው።  
የኮቪድ ውረርሺኝ በትምህርት ሂደቱ ላይ የፈጠረው መስተጓጎል እንዳይቀጥል ለማድረግ መሰራት ያለበት ስለመሆኑም  የአውሮፓው የዓለም  የጤና ድርጅት ሀላፊ በመገለጫቸው አውስተዋል። በኮቪድ ምክኒያት የትምህርት ቤቶች መዘጋት በተለይ በወጣቶች ስነ ልቦናና አስተዳደግ ላይ ተጽኖ ማሳደሩን በመጥቀስም፤ ዘንድሮ አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተደረገና ክትባቱንም በማስፋፍት መደበኝው ትምህርት እኒዲቀጥል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል  ድምጽ ባለፉት 20 ወራቶች ልጆቻችን በተለይም በኢንተርኔት ትምህርታቸውን መከታተል ያልቻሉት ብዙ ተሰቃይተዋል፤ ለኧምሮ መታወክም ተጋልጠዋል። የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓው ክፍልና የኒሴፍ አስፈላጊዎች እርምጃዎች ተወስደው ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ጥሪ እናቀርባለን። በቅድሚያ ግን መምህርንና  የትምህርት ባለሙያዎችን እንዲሁም ከ12 አመት በላይ የሆኑትንና በተይም የተለየ ችግር ያለባቸውን ልጆች ኢላማ ያደረገ የክትባት መርሀ ግብር መዘርጋትና መተግበር ያስፈልጋል  በማለት በአሁኑ ወቅት ለትምህርት ቤቶች  መከፈትና ለመደበኛው ትምህርት መጀመር መሟላት የሚኖርቫቸውን አስገንዝበዋል። 

ገበያው ንጉሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች