የኮርያ ዘማቾች ትዉስታ | ባህል | DW | 25.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የኮርያ ዘማቾች ትዉስታ

የኮርያ የዕርስ በርስ ጦርነት ካበቃ ዘንድሮ ስድሳ ዓመቱን ያዘ። በኮርያ የእርስ -በርስ ጦርነት ጊዜ በተመድ የኮርያ ዘማች ጦር ውስጥ በመሰለፍ ከደቡብ ኮርያዉያን ጋር የተሰለፉት ኢትዮጵያዉያን፤ የኮርያ ዘማቾች ማህበር በሚል ጥላ ስር ከተሰባሰቡ 20 ዓመት በላይ እንደሆናቸዉ ይናገራሉ።

የደቡብ ኮርያ መንግስት፤ በተመድ የኮርያ ዘማች ጦር ውስጥ ለተሰለፉ እና አሁን በህይወት ለሚገኙ ወደ 340 ለሚጠጉ አባት ዘማች ኢትዮጵያዉያን ድጋፍ በማድረግ ላይ ሲሆን ለዘማች ልጆችና የልጅ ልጆችም ከአለፈዉ ዓመት ጀምሮ የነጻ ትምህርት እድል በመስጠት ላይ ይገኛል።

በ21 ዓመታቸዉ ወደ ኮርያ የዘመቱት እና የአሁኑ የኮርያ ዘማቾች ማህበር ሊቀመንበር ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ስለማህበሩ እንዲህ ይገልጻሉ፤ በኮርያዉ ጦርነት ላይ ከዘመቱት መካከል ሻምበል ይልማ በላቸዉ ይገኙበታል፤ ሻንበል በላቸዉ፤ ከኢት ዮጵያ ተነስተን ኮርያ እስክንደርስ ወደ ሃያ ቀናት እንደፈጀባቸዉ ያስታዉሳሉ።

ከጅቡቲ ተነስተን በ22 ቀናችን ቱሳን ደረስን ያሉን ሻንበል ይልማ በላቸዉ ፤ ቱሳን የኮርያ ባህር በር መሆኑን አጫዉተዉናል። የኮርያ ዘማቾች ማህበር ሊቀመንበር ኮሎኔል መለሰ ተሰማ በበኩላቸዉ በኮርያ ደርሰን የመጀመርያዉ የኮርያ ገጠመኛችን ይላሉ በማስታወስ፤

በኮርያ ጦርነት ኢትዮጵያ ከ6ሺህ በላይ ወታደሮችን ማሳተፉዋን የገለጹልን ኮሎኔል መለሰ ተሰማ፤ በኮርያ የበጋ ልብስ እና የክረምት ልብስ መለያየቱን፤ ቀን በቀን የምንበላዉ እንጀራ በኮርያ አለመኖሩን አዉቀናል።

የኮርያዉያን ባህል ከኢትዮጵያዉያኑ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ አግንቸዋለሁ ያሉን ሻምበል ይልማ በላቸዉ ኮርያ ሳለን የእረፍት ግዜአችንን ጃፓን ድረስ እየሄድን እናሳልፍ ነበር ብለዉናል።

የማህበሩ ፕሬዝደንት እንደ ይልማ በላቸዉ ከደቡብ ኮርያ በተገኘዉ የነጻ ትምህርት እድል ባለፈው አመት 60 ተማሪዎች ወደ ኮርያ ሄደዉ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ 140 ተማሪዎችን ለመላክ ዝግጅቱን አጠናቀናል ብለዋል ። ከነዚህ መካከል የ 25 ዓመቱ ወጣት ሚኪያስ የኋላእሸት ይገኝበታል።

ለአንድ ዓመት የሞያ ስልጠና ወደ ኮርያ ለመሄድ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ የነገረን ወጣት ሚኪያስ የኋላ እሸት በወር ሶስት መቶ ዶላር እየተከፈለዉ ወደ አንድ ዓመት ተኩል ግድም የሞያ ትምህርቱን እንደሚከታተል አጫዉቶናል።

ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በነበረው የኮርያ እርስ በርስ ጦርነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካይነት ወደዚያው ከዘመቱ አገራት መካከል ለኢትዮጵያዉያን ብቻ የመታሰብያ ሐዉልት ቆሞ ይገኛል፤ ያሉን የኮርያዉ ዘማች ኮሎኔል መለሰ፤ ትዝ የሚለኝን የኮርያ ዜማ ላዚምላችሁ ብለዉ አዚመዉልናል፤ ለቅንብሩ መሳካት ቃለ ልልስ የሰጡትን በሙሉ በዶቼ ቬለ ስም እናመሰግናለን።

ሙሉ ቅንብሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic