የኮሬንቲ እጥረት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 11.08.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኮሬንቲ እጥረት በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የመብራት ኃይል ባለስልጣን የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት እየጎዳ ያለው የኃይል እጥረት እና እጥረቱን ተከትሎ የተፈጠረውን ኃይል በፈረቃ የማዳረሱን ስራውን ለጊዜው እንደሚቀጥልበት ዛሬ አስታወቀ።

default

የባለስልጣኑ የግንኙነት ክፍል ዋና መኮንን አቶ ምስክር መኮንን ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት የክረምቱ ዝናብ ዘግይቶ በመጀመሩ፡ ከጀመረም በኋላ መጠኑ የተጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ የኃይል ማመንጨቱ ስራው በተጠበቀው ፍጥነት ሊከናወን አልተቻለም። የተሻለ የውኃ መጠን በተጠራቀመበት በተከዜ የኃይል ማመንጫ ግድብ ካሉት ከአራቱ የማመንጫ ሞተሮች በአንዱ ሰባ አምስት ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት የሙከራ ስራ እየተካሄደ መሆኑን አቶ ምስክር አክለው ገልጸዋል።

ታደሰ እንግዳው /አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic