የኮሪያ ልሳነ ምድር ዉጥረት እና የአዉሮጳ ሕብረት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.09.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኮሪያ ልሳነ ምድር ዉጥረት እና የአዉሮጳ ሕብረት

የሕብረቱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ በተጨማሪ ማዕቀብ መቅጣት አለበት።የዚያኑ ያክል ማዕቀቡ  የፒዮንግዮንግ ባለሥልጣናትን ወደ ድርድር እንዲመለሱ ከማስገደድ ያለፈ ዓላማ  ሊኖር አይገባም ባይ ናቸዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:59
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:59 ደቂቃ

የኮሪያ ልሳነ ምድር ዉጥረት እና የአዉሮጳ ሕብረት

ሰሜን ኮሪያ ከዩናይትድ ስቴትስ፤ ከደቡብ ኮሪያና ከጃፓን ጋር የገጠመችዉን የዉጊያ ዛቻ እና ፍጥጫ ለማስቆም ቅጣት ከድርድር የቀየጠ መፍትሔ እንዲፈለገ የአዉሮጳ ሕብረት ጠየቀ።የሕብረቱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ በተጨማሪ ማዕቀብ መቅጣት አለበት።የዚያኑ ያክል ማዕቀቡ  የፒዮንግዮንግ ባለሥልጣናትን ወደ ድርድር እንዲመለሱ ከማስገደድ ያለፈ ዓላማ  ሊኖር አይገባም ባይ ናቸዉ።በኮሪያ ልሳነ ምድር የሚደረገዉ የዉጊያ ዝግጅት፤ የወታደር እና የጦር መሳሪያ ክምችት እንዲቆምም ሕብረቱ ጠይቋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic