የኮምፓሽን ፍሬዎች | ባህል | DW | 22.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የኮምፓሽን ፍሬዎች

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዶች፤ ለሌሎች ፍቅር መስጠት የሚል አላማ ይዘው ይንቀሳቀሳሉ። ጠያቂ የሌላቸው ኅሙማንን፣ እስረኞችን እና የጎዳና ተዳዳሪዎችን እያፈላለጉ እና እየጎበኙ በበጎ ፍቃደኝነት ስለሚሠሩት ሥራ ያብራራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:24
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:24 ደቂቃ

የኮምፓሽን ፍሬዎች

የ28 ዓመቱ ፍፁም ፀጋዬ፤ እና የባልደረቦቹ አላማ «ፍቅርን ላጡ ሰዎች ፍቅርን ማካፈል» ነው። በትርፍ ጊዜያቸው ከሚሠሩት የበጎ አድራጎት ስራ አንዱ የጎዳና ተዳዳሪዎችን መርዳት ነው። ሰላማዊት ደስዬ፤ ከበጎ አድራጊዎቹ ወይም የኮምፓሽን ፍሬዎች (Fruits of compassion) አንዷ ናት። ወጣቶቹ አብረው መስራት ከጀመሩ ሶስት ዓመት ሆኗቸዋል። ሰሞኑን በጎ አድራጊዎቹ ከሚተባበርት ወጣት አንዷ ደግሞ የ 16 ዓመቷ ቃልኪዳን ናት። ጎዳና ላይ ስትኖር 3 ዓመታት ተቆጥረዋል። ወጣቷን ለጎዳና የዳረጋት የእናቷ አይነ ስውር መሆን እና ችግር ነው።

ሰላማዊትም ትሁን ፍፁም ዛሬ ለሚያደርጉት የበጎ አድራጎት ስራ አስተዳደጋቸው ትልቅ ሚና እንደተጫወተ ገልጸውልናል። ሁለቱም ያደጉት ኮምፓሽን በተባለ ድርጅት ድጋፍ ነው። ፍፁም ዛሬ በኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማህንዲስ ሲሆን ሰላማዊት ደግሞ የልብስ ነዳፊ ወይም ዲዛይነር ናት።

በበጎ አድራጎት ስራው የተሰማሩት ፍፁም እና ሰላማዊትም ይሁኑ ሌሎች ባልደረቦቻቸው ለረዥም ዓመታት የሚተዋወቁ እና ኮምፓሽን ድርጅት በተባለው ድጋፍ ተደርጎላቸው ያደጉ ልቾች ብቻ ናቸው። ለሌሎች ፍቅር መስጠት የሚል አላማ ይዘው ከሚንቀሳቀሱት እና ራሳቸውን የኮምፓሽንፍሬዎች ብለው ከሚጠሩት ወጣቶች መካከል ፍፁም ፀጋዬ እና ሰላማዊት ደስዬ ስለ በጎ አድራጎት ስራቸው ያካፈሉንን ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic