የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 03.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር መግለጫ

ባለፉት ሶስት ወራት ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ 5.6 ሚሊዮን ህዝብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ዛሬ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:42

የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር መግለጫ

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ዛሬ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሀገር ውስጥ ና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትሩ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል በኦሮምያ እና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታት በመደረግ ላይ ያለውን ጥረት አስረድተዋል ሚኒስትሩ ሁለቱን ክልሎች እና የሀገር ሽማግሌዎችን ያሳተፈ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል ።። ባለፉት ሶስት ወራት ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ 5.6 ሚሊዮን ህዝብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ አለው ። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሃመድ 

Audios and videos on the topic