የክሬታዉ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ጉባዔ | ዓለም | DW | 23.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የክሬታዉ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ጉባዔ

ባለፈዉ እሁድ ክሬታ ግሪክ የጀመረዉ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጉባዔ ዉጥረት እንዳጠላበት ተነገረ። ምክንያቱ ደግሞ ወቅታዊዉ የዓለም የፖለቲካ ርምጃ በአብያተ ክርስትያናቱ ላይ ስምምነት እንዲመጣ አልጋበዘም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:55

የአብያተ ክርስቲያናት ጉባዔ በክሬታ

የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀርጤስ ግሪክ ውስጥ በሚካሄደው የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጉባዔ ላይ አትገኝም በመባሉ ከመጀመርያዉም ነቀፋ እንደደረሰባት ይታወቃል። የጀርመን ኦርቶዶክስ ጳጳሳት ጉባዔሊቀመንበር ለጉባዔዉ ወደ ክሬታ ወይም ቀርጤስ ከመሄዳቸው በፊት በሰጡት መግለጫ የሩስያ ቤተ-ክርስቲያን በጉባዔው ባለመገኘት «ከቅዱስ ቤተ-ክርስቲያናችን የጋራ ፍላጎትና ጥቅም ይልቅ የብሔራዊ የተናጠል ሀገርን ፍላጎት እና የበላይነት ቅድምያ ሰጥታዋለች» ሲሉ ወቅሰዋል። የቡልጋርያ እና ጆርጂያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኮች ከ 50 ዓመት በፊት እንዲካሄድ በታቀደው ታሪካዊ የኦርቶዶክስ ምክር ቤት ጉባዔላይ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደማትገኝ ተናግረዋል። የጀርመን ወንጊላዊት ቤተ ክርስቲያን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ሩስያ ከዓለም ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ግማሽ ያህሉ የሚገኙባት ሀገር ናት።

የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርርስቲያን ምዕመን ብዛት ወደ 160 ሚሊዮን ይጠጋል። የሩስያ ኦርቶዶስክ ቤተ-ክርስቲያን በጉባዔው ላይ እንደማትግካፈል ከማሳወቋ በፊት መላው የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ካልተካፈሉ ጉባዔው ትርጉም አይኖረውም በማለት ስታንገራግር ነበር።

ከዘመናት በኋላ ለስምንተኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለዉ በዚህ ጉባዔ ላይ መሳተፍ ከነበረባቸዉ የ14 ሃገራት የኦርቶዶክስአብያተክርስቲያናትመካለል የአራት ሃገራት የኦርቶዶክስአብያተክርስቲያናትአለመገኘታቸዉ ታዉቋል። ሩስያን ጨምሮ ቡልጋርያ ሶርያና የጆርጅያ አብያተ ክርስትያናት በዚህ ጉባዔ ላይ ያለመሳተፍቸዉ ዋና ምክንያት በፖለቲካና ሥልጣን ንትርክ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ። በእዚህ ጉባዔ ኢትዮጵያ ተሳታፊ ትሆን? በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ዋና ተጠሪ ሊቀነ ካህናት ዶክተር መራዊ ተበጀን በክሬታ ስለተጀመረዉ ጉባዔ ጠይቀናቸዋል።


አዜብ ታደሰ


አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic